Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Tew Semagn şarkı sözleri

Sanatçı: Hamelmal Abate

albüm: Kemsha


ተዉ ስማኝ ስማኝማ ዛሬ
መል እንጂ ንገረኝ አንተ ዝም አትበለኝ
ምንድነዉ ይሄ እንግዳ ፀባይ
ያለመደብህ ማምረርህ በኔ
ከመቼ ወዲያ ነዉ ከመች ወዲህ ደሞ
በእኔና አንተ መሃል አስታራቂ ቆሞ
ከየት የመጣ ነዉ ይሄ አዲስ ፀባይ
ገና በእኔና አንተ ያምኑናል ወይ

በፍቅር ዘመንህ በፍቅር ዘመኔ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አስቸግሬ ለአንተ አስቸግረህ ለኔ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አልፎ ከኔና አንተ ግዜዉ የጥላችን (በል ንገረኝ ዛሬ)
ያዉቃል እንዴት ሸምጋይ ቆሞ መሃላችን (በል ንገረኝ ዛሬ)
በፍቅር ዘመንህ በፍቅር ዘመኔ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አስቸግሬ ለአንተ አስቸግረህ ለኔ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አልፎ ከኔና አንተ ግዜዉ የጥላችን (በል ንገረኝ ዛሬ)
ያዉቃል እንዴት ሸምጋይ ቆሞ መሃላችን (በል ንገረኝ ዛሬ)
ለሚያዉቁን በሙሉ ለዘመድ ለወዳጅ
አስታራቂ ሸምጋይ እንዳልክ አማላጅ
ደሞ ከመች ወዲያ ይሉኛል እያልኩኝ
ለምንም ሳልነግር አፍኜዉ ከረምኩኝ
መጣላታችንን (ማን ይኖራል) ዞረን ብናወራ
የአስታራቂ ያለህ (ማን ይኖራል) ብለን ሰዉ ብንጠራ
እዉነት ነዉ የሚለን (ማን ይኖራል) ማን ይኖራል ከቶ
በዚ አያዉቅምና (ማን ይኖራል) ስማችን ተነስቶ
መጣላታችንን (ማን ይኖራል) ዞረን ብናወራ
የአስታራቂ ያለህ (ማን ይኖራል) ብለን ሰዉ ብንጠራ
እዉነት ነዉ የሚለን (ማን ይኖራል) ማን ይኖራል ከቶ
በዚ አያዉቅምና (ማን ይኖራል) ስማችን ተነስቶ

የመሸ የጨለመዉ ነግቶ
የጠቆረዉ ሰማይ በብርሃን ፈክቶ
ፍቅራች ያብባል ዳግመኛ
አረ አንለያይም መቼም ቢሆን እኛ
የተፈጠረብንን ይዘን አዲስ ፀባይ
ዉስጠ ገመኛችን ሲወጣ አደባባይ
እንዴት አያሳዝን እንዴት አያስደንቅ
የጥንቱ ፍቅራችን ዛሬ ከኛ ሲርቅ

ተስማምተን በፍቅር ለመኖር አንድ ላይ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አልረፈደም ዛሬም አልገባችም ፀሃይ (በል ንገረኝ ዛሬ)
ይቅር ለመባባል ካሰብን በቀና (በል ንገረኝ ዛሬ)
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና (በል ንገረኝ ዛሬ)
ተስማምተን በፍቅር ለመኖር አንድ ላይ (በል ንገረኝ ዛሬ)
አልረፈደም ዛሬም አልገባችም ፀሃይ (በል ንገረኝ ዛሬ)
ይቅር ለመባባል ካሰብን በቀና (በል ንገረኝ ዛሬ)
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና (በል ንገረኝ ዛሬ)
እንዲህ ነበር እንዴ የኛ ፍቅር ድሮ
የሚያጨካክነን ምን መጣ ዘንድሮ
ወሬ አራጋቢዉን ይቅርብን አንስማ
የሚያባብስ እንጂ የለም የሚያስማማ
ስለኛ በኩራት (ማን ይኖራል) የመሰከሩት
ተምሳሌተ ፍቅር (ማን ይኖራል) ሲሉን የነበሩት
ያ ፍቅራችን ዛሬ (ማን ይኖራል) እንዲህ በመሆኑ
እንኳንስ የሰሙ (ማን ይኖራል) ያዩን መች አመኑ
መጣላታችን (ማን ይኖራል) ዞረን ብናወራ
የአስታራቂ ያለህ (ማን ይኖራል) ብለን ሰዉ ብንጠራ
ምንም የለምና (ማን ይኖራል) እዉነት ነዉ የሚለን
እኛዉ እንስማማ (ማን ይኖራል) ይቅር ተባብለን
ይቅር ለመባባል ካሰብን በቀና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና
ይቅር ለመባባል ካሰብን በቀና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ ደንገዝገዝ አለ እንጂ
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ ደንገዝገዝ አለ እንጂ
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ ደንገዝገዝ አለ እንጂ
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ ደንገዝገዝ አለ እንጂ
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና
ደንገዝገዝ አለ እንጂ ደንገዝገዝ አለ እንጂ
ደንገዝገዝ አለ እንጂ አልጨለመም ገና

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar