Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Enetarek şarkı sözleri

Sanatçı: Hamelmal Abate

albüm: Kemsha


እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ መሪ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ ብሉይ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል

አካል ገላ ገላዬ
የልቤ ሰው ትዝታዬ
ሆድ አስባሰኝ ናፍቆቴ
አንታረቅ በሞቴ
አካል ገላ ገላዬ
የልቤ ሰው ትዝታዬ
ሆድ አስባሰኝ ናፍቆቴ
እንታረቅ በሞቴ
እንዲ ሲቀጣ ልቤ በፀፀት
አያባራም ወይ
የኩርፊያ ክረምት
የማትመጣልኝ ዞረህ በበሩ
እንዲ ሩቅ ነው ወይ የኩርፊያ አገሩ

አስታራቂ ጠፍቶ አንድ እኛን ሀይ ባይ
ቀረን ባዋጅ ወተን በየአደባባይ
ምነዋ ከፍቶኝ ሳድር
ብትለኝ ይቅር ለግዜር
ሁሉን ቻይ ጠፍቶ እንጅ ጥርስ ነክሶ ከንፈር
የሚያደርሰን እዚህ ነገሩስ አልነበር
ምነዋ ልብህ በተራ
ቢጠለል ደጉ ከዚራ
በፍቅር ዓለም ሰው አብሮ ከኖረ
ያለ ነው ፀቡ በኛ አልተጀመረ
አይለያዩም መስከረምና ዓደይ
እስቲ እኛም ታርቀን እንሁን አንድ ላይ
ኧሀ
አይናፍቅምና የማያውቁት ሀገር
ይመለስ ንገረው የወሰደህ እግር
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ ብሉይ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ መሪ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል

አካል ገላ ገላዬ
የልቤ ሰው ትዝታዬ
ሆድ አስባሰኝ ናፍቆቴ
አንታረቅ በሞቴ
አካል ገላ ገላዬ
የልቤ ሰው ትዝታዬ
ሆድ አስባሰኝ ናፍቆቴ
እንታረቅ በሞቴ
እንዲ ሲቀጣ ልቤ በፀፀት
አያባራም ወይ
የኩርፊያ ክረምት
የማትመጣልኝ ዞረህ በበሩ
እንዲ ሩቅ ነው ወይ የኩርፊያ አገሩ

ልሂድ ሰው ካለማ ቃል እየቆጠረ
ያብሮ መኖር ስሙ ፍቅር ባልነበረ
ምነው ብትለኝ ይቅር
ሆድ አይሰፋም ወይ ካገር
ይቅር ባይ ካልሆነ አፍቃሪ ካንጀቱ
ግንጥል ጌጥ ብቻ ነው ቀለበት ለጣቱ
ምነው ብትለኝ ይቅር
ሆድ አይሰፋም ወይ ካገር
በፍቅር ዓለም ሰው አብሮ ከኖረ
ያለ ነው ፀቡ በኛ አልተጀመረ
አይለያዩም መስከረምና ዓደይ
እስቲ እኛም ታርቀን እንሁን አንድ ላይ
ኧሀ
አይናፍቅምና የማያውቁት ሀገር
ይመለስ ንገረው የወሰደህ እግር
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ ብሉይ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ መሪ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
አይናፍቅምና የማያውቁት ሀገር
ይመለስ ንገረው የወሰደህ እግር
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ ብሉይ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
እንደ ኦሪት ትዛዝ ልክ እንደ መሪ ቃል
እንዴት ሰው ከ ቂም ጋር በፍቅር ይወድቃል
አይናፍቅምና የማያውቁት ሀገር
ይመለስ ንገረው የወሰደህ እግር

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar