ሳጣዉ ነዉ እኔስ የሚከፋኝ ቁም ነገር ሲጠፋኝ
ሳጣዉ ነዉ ቅር ቅር የሚለኝ ሀሳብ የሚገለኝ
ወዴት ይሆን ዘንድሮስ የራቀኝ
ያ የማዉቀዉ ቁም ነገር ናፈቀኝ
የጎደለኝ አንድ ነገር አለ
ያደግንበት ቁም ነገር የት ዋለ
♪
ዋሽቶ የሚያጣላ በበዛበት ዘመን
ሲገኝ ደስ ያሰኛል በቃሉ ሚታመን
እንኳን በዚህ ግዜ ዉሉ በጠፋበት
ወትሮም ቁም ነገር ነዉ የዚች አለም ዉበት
ከአፉ ማር ጠብ የሚል ሲጫወት
እንዴት አይናፍቅም ሰዉ ማግኘት
የታል ሽማግሌዉ አስታራቂቂዉ
እድሜ ያስተማረዉ ብዙ አዋቂዉ
እህ አረ የታል የታል
እህ አረ የታል የታል
እህ አረ የታል የታል
እህ አረ የታል የታል
ከሰዉ ተዋዶ ፍቅር ቢቀድም
ቁም ነገር ሸሽቶ የትም አይሄድም
ለችግር ደራሽ ለብሶተኛ
አድርገን ጌታ ቁም ነገረኛ
♪
ሳጣዉ ነዉ እኔስ የሚከፋኝ ቁም ነገር ሲጠፋኝ
ሳጣዉ ነዉ ቅር ቅር የሚለኝ ሀሳብ የሚገለኝ
ወዴት ይሆን ዘንድሮስ የራቀኝ
ያ የማዉቀዉ ቁም ነገር ናፈቀኝ
የጎደለኝ አንድ ነገር አለ
ያደግንበት ቁም ነገር የት ዋለ
♪
እምት ያስተማረዉ ሚስጥሩ የገባዉ
አያጠፋም ጊዜ በረባ ባልረባዉ
ያደግነንበት ናህል የተቃኘንበት
ምን አለ ይባላል ካለስተዋልንበት
ለደግ የመረጠዉ ለቁም ነገር
አንጀቱ ሚርስ ነዉ ሰዉ ሲፋቀር
አንተ ትብስ አንቺ መባባሉ
አረ ወዴት ጠፉ ወዴት ዋሉ
እህ አረ ወዴት ወዴት
እህ አረ ወዴት ጠፉ
እህ አረ ወዴት ወዴት
እህ አረ ወዴት ዋሉ
ከሰዉ መዋደድ ፍቅር ቢቀድም
ቁም ነገር ሸሽቶ የትም አይሄድም
ለችግር ደራሽ ሰዉ ያርገንና
ሳናጣ እንሙት የአምላክ ምስጋና
ሳናጣ እንሙት ከአምላክ ምስጋና
ሳናጣ እንሙት ከአምላክ ምስጋና
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri