Kishore Kumar Hits

The Roha Band - Gedam Endegeba şarkı sözleri

Sanatçı: The Roha Band

albüm: The Reunion


ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ሰፈሩንም ትቼ ልራቀው ልሂደው
ሰፈሩንም ትቼ ልራቀው ልሂደው
ያንድ ሰው ትዝታ ልቤን እየናደው
መቼ ይጠፋኝ ነበር መርታት እንደሌላው
መቼ ይጠፋኝ ነበር መርታት እንደሌላው
ቀኑ አላልፍ አለ እንጂ መውደድ እየመላ()
ይህ ፍቅር መንደሩን በኔ ላይ ከትሞ
ይህ ፍቅር መንደሩን በኔ ላይ ከትሞ
ያንገላታኝ ጀመር ልቤ በሰው ታሞ
ያንገላታኝ ጀመር ልቤ በሰው ታሞ
ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ምን ይሆን ብልሀቱ ኧረ መውደድ ባሰ
ምን ይሆን ብልሀቱ ኧረ መውደድ ባሰ
ባልመው ባስበው የልቤ አልደረሰ
ከሆዴ ገባና ካንጀቴ ላይ ውሎ
ከሆዴ ገባና ካንጀቴ ላይ ውሎ
ነፍሴንም ገዝቷታል ፍቅር ለሷ ብሎ
ይህን ቀበቶዬን ብተወውስ ምነው
ይህን ቀበቶዬን ብተወውስ ምነው
የማይሸመቀቅ የማይጠብቅ አንጀቶ ነው
የማይሸመቀቅ የማይጠብቅ አንጀቶ ነው
ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ገዳም እንደገባ እንደመነኮሰ መራቅሽን እያየ አሀ አሀሀ
አይኔ እምባ አፈሰሰ
ውበቷ በልቤ እየተሞካሸ
ውበቷ በልቤ እየተሞካሸ
ሳላያት ይነጋል ቀኑም እየመሸ
ባልንጀራ አልጠራ የልቤን አልመክር
ባልንጀራ አልጠራ የልቤን አልመክር
ሰው ጠፍቶኛል ብዬ አልወጣም ከምክር ()
ያበጃጁት መውደድ ያሰሩት በመላ
ያበጃጁት መውደድ ያሰሩት በመላ
ሲፈርስ ያሳዝናል ሲጠፋበት መላ
ሲፈርስ ያሳዝናል ሲጠፋበት መላ
ሲፈርስ ያሳዝናል ሲጠፋበት መላ
ሲፈርስ ያሳዝናል ሲጠፋበት መላ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar