ይበራል ልቤ ካንቺው ጋራ
ወንዙን ተሻግሮ ያን ተራራ
ይዞራል ልቤ ካንቺ መንደር
ሲጫዎት ሊያመሽ ወይ ለማደር
ከአለቱ ቅብ ዉሃ ወፎች ካዜሙበት
በቀስተደመና ህብሩ ካማረበት
ከሸጋዎች ሰፈር ካለሽበት ቦታ
ገሰገሰ ልቤ ይዞልሽ ሰላምታ
አያ አያ አያ
አያ አያ አያ
????
እኔ አልመኝም ከሌላ
አንቺ የልቤ ወለላ
እስኪ ንገሪኝ በመላ
በመላ
እስኪ ንገሪኝ በመላ
በመላ
እስኪ ንገሪኝ በመላ
(ሙዚቃ)
አያ አያ አያ
አያ አያ አያ
(ሙዚቃ)
ይበራል ልቤ ካንቺው ጋራ
ወንዙን ተሻግሮ ያን ተራራ
ይዞራል ልቤ ካንቺ መንደር
ሲጫዎት ሊያመሽ ወይ ለማደር
(ሙዚቃ)
በተንጣለለው መስክ ጨረቃ ፈንጥቃ
በሰማይ ከዋክብት ተጅባና ደምቃ
ከለምለሙ ሰፈር ከሸጎቹ መንደር
ሲጫዎት ያመሻል ልቤ ሲደራደር
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
(ሙዚቃ)
ትዝታ ባየር ተጉዞ
ናፍቆት ሰቀቀን ጎዝጉዞ
መልዕክት ሰላምታዬን ይዞ
ይመጣል ልቤ ተጉዞ
ተጉዞ
መልዕክት ሰላምታውን ይዞ
ተጉዞ
መልዕክት ሰላምታውን ይዞ
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
አያ አያ አያ አያ አያ አያ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri