Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Ferejign şarkı sözleri

Sanatçı: Dawit Mellesse

albüm: Andiken


እስኪ በይ ፍረጂኝ ቅጣቴ አልበዛም ወይ
አንቺንም ኑሮንም ማጣት ቀላል ነው ወይ
አላውቅም ነበረ በኔው ግፍ መዋሌን
አንቺን ሳጣሽ መዋለሌን

አለምድ አለ የኔ ገላ
ምን ይሻላል አንቺ የሌላ
ሲዋደዱ መተጣጣት
ይህ እኮ ነው ክፉ ቅጣት
ያለወቅቱ አጊኝተሺኝ
በስህተት አመለጥሺኝ
ይከፋኛል ሳስታውሰው
መሆንሽን የሌላ ሰው

ለምን የፍቅር እጣ ሁሌ ይጠማል
አሁን የሚጣጣም መች ይገጥማል
እኔ ያላንቺ መሸ ነጋ ምን እዳዬ
አንቺ ጎለሽ ከጓዳዬ
የኔ ልቤም ቤቴም ዝግ ነው በሩ
ፍቅሬ አንቺ ነግሰሽ በመንበሩ
ኧረ ኧረ እጦቴን ተመልከቺ
እስረኛሺን ልቤን ፍቺ

እስኪ በይ ፍረጂኝ ቅጣቴ አልበዛም ወይ
አንቺንም ኑሮንም ማጣት ቀላል ነው ወይ
አላውቅም ነበረ በኔው ግፍ መዋሌን
አንቺን ሳጣሽ መዋለሌን

ልብ ያላየ አያረካ
በእጅ ያልያዙት አያስመካ
ሰው ባሰበው መች ይውላል
አንዱን ሲያገኝ ሌላ ይጎላል
የሰው መሆን ሆድ ቢያስብስም
አድናቆቴ አይቀንስም
ይህ ይመጣል ብዬ አላውቅም
የቅጣት ቀን ጭንቁ አያልቅም

ናፍቆትሽ ትዝታሽ ልቤን አስጨነቀው
መንፈሴን አወከው
እንዴት ነው የማይሽ የት ነው የማገኝሽ
እባክሽ ልወቀው
የኔ ገላ አይኔ ራበሽ ሆዴን ባሰው
ፍቅሬ አትተኪም አንቺ በሰው
አለው ስለራቅሺኝ ተንገብግቤ
አንቺ ጠፍተሽ ካጠገቤ
ምነው ምነው ሆዴን ሆድ ባይብሰው
ምን ያረጋል እኔም የሰው አንቺም የሰው
ኧረ ጭንቄን ባክሽ ትረጂልኝ
ሰላም ኑሮ ፍቀጂልኝ

ሰላም ኑሮ ፍቀጂልኝ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar