Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Yaken Yemetana şarkı sözleri

Sanatçı: Dawit Mellesse

albüm: Andiken


እኔ ስከተልሽ ትዪኛለሽ ችላ
ፍቅር ዙሩ ደርሶ የፊት ወደኋላ
ይህም ቀን ያልፍና ለኔ ያደላና
ጠቅልዬ አስገብቼ የኔ እልሽና
ያ ቀን ይመጣና
በተራሽ ቀን መቶ ናፈከኝ ብለሺኝ
ዋ ብለሺኝ ዋ ብለሺኝ
እድሉ ደርሶብኝ አንቺም ፈልገሺኝ
(ፈልገሺኝ ፈልገሺኝ)
ያልመጣሽ እንደሆን ከደጅ ከበራፌ
እኔ አይደለሁማ ከቀረው ከንፌ
አብረን እያለን የመጣ ለት
የያዘ ለት የኔስ እውነት
ቀኑ ቢመሽ ሌቱ ነግቶ
ባየር በእግር ሁሉን ትቶ
ወዳጅ ዘመድ ተሰናብቶ
ካሳብ ርቆ ከሰው ጥፍቶ
አንቺማ ማቀፍ በር ዘግቶ
አለም ማየት ነው ኑሮን ረስቶ
እኔ ስከተልሽ ትዪኛለሽ ችላ
ፍቅር ዙሩ ደርሶ የፊት ወደኋላ
ይህም ቀን ያልፍና ለኔ ያደላና
ጠቅልዬ አስገብቼ የኔ እልሽና
ያ ቀን ይመጣና
ይቆጭሻል ገና ሳታዪኝ ማደርሽ
ናፈኩህ ትያለሽ ቀርቶ መግደርደርሽ
ማፍቀር መለመኔን ገፍተሽ ስለወጣሽ
ፀጉር ከምላሴ ለምነሽ ካልመጣሽ
ያ ቀን መቶ ፈልገሺኝ
ልይህ ብለሽ ጠይቀሺኝ
በጄ ገብተሽ አስፈርሜ
ዕውን ሆኖ ምኞት ህልሜ
ጥጋብ መቶ ራቤ አልፎ
ገላዬ አርፎ ክንዴም አርፎ
ምን ተይዞ ከዚ ወዲያ
አንቺም ወዲ እኔም ወዲያ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar