Tsegaye Eshetu - Nigat şarkı sözleri
Sanatçı:
Tsegaye Eshetu
albüm: Nigat
ንጋት ሲለያየን አብረን አድረን
ትተሽብኝ ያንን ጣፋጭ ጠረን
እስከምንገናኝ በምሽቱ
አይጣል አይጣል ያሰኛል ናፍቆቱ
አቤት ስታስጨንቂ ከጎኔ ስትርቂ
እኔስ ከጉያሽ ርቄ መከራ ነው ስንቄ
♪
የኔ ጣፋጭ የፍቅር ወለላዬ
ጥለሽብኝ ትዝታን በላዬ
አልቻለም ገላዬ አልቻለም ገላዬ
አልቻለም ገላዬ አልቻለም ገላዬ
♪
ንጋት ሊያበስሩ ወፎቹ ሲንጫጩ ኩኩሉ ሲል ዶሮ
እንቅልፍ እየነሳ ያነጫንጨኛል አመሌ ቀይሮ
መሽቶ ስንገናኝ የሚሰማኝ ስሜት የማገኘው ደስታ
ነግቶ ስንለያይ ህልም ይሆንብኛል በቀኑ ትዝታ
ስቃዬ ነው ለኔማ መርዶዬ ነው ለኔማ የወፎቹ ዜማ
የወፎቹን ዜማማ የሞላለት ሰው ይስማ አይጥመኝ ለኔማ
አልውልም ችዬ አላድችም ችዬ
ትዝታ ናፍቆት ሃሳብ አዝዬ
አልውልም ችዬ አላድችም ችዬ
ለአንድ ቀን እንኳን ሳጣሽ አንችዬ
♪
ንጋት ሲለያየን አብረን አድረን
ትተሽብኝ ያንን ጣፋጭ ጠረን
እስከምንገናኝ በምሽቱ
አይጣል አይጣል ያሰኛል ናፍቆቱ
አቤት ስታስጨንቂ ከጎኔ ስትርቂ
እኔስ ከጉያሽ ርቄ መከራ ነው ስንቄ
♪
የኔ ጣፋጭ የፍቅር ወለላዬ
ጥለሽብኝ ትዝታን በላዬ
አልቻለም ገላዬ አልቻለም ገላዬ
አልቻለም ገላዬ አልቻለም ገላዬ
♪
ሰማይና ምድር እየተላቀቁ ጎህ እየቀደደ
መሄድሽን ሳስበው ያንቀጠቅጠኛል ውስጤ እየበረደ
ደና ዋል የሚለው የመሰናበቻ ቃሉን እንዳልሰማ
ስትሄጂ ገለሽን ስትመጪ ባዳንሽኝ አልኩኝ አሁንማ
ስቃዬ ነው ለኔማ መርዶዬ ነው ለኔማ የወፎቹ ዜማ
የወፎቹን ዜማማ የሞላለት ሰው ይስማ አይጥመኝ ለኔማ
አልውልም ችዬ አላድችም ችዬ
ትዝታ ናፍቆት ሃሳብ አዝዬ
አልውልም ችዬ አላድችም ችዬ
ትዝታ ናፍቆት ሃሳብ አዝዬ
አልውልም ችዬ አላድችም ችዬ
ለአንድ ቀን እንኳን ሳጣሽ አንችዬ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri