Tsegaye Eshetu - Kijet şarkı sözleri
Sanatçı:
Tsegaye Eshetu
albüm: Nigat
ለሊት አባኖኝ ቅዥትዋ
ጉዴን ሰማው ካንደበትዋ
የውን ታሪክ ነው ልብ ወለድ
የስዋ በኔ ላይ ሌላ ሰው መውደድ
እንዳልሰማ ሰው አላልፈው
የደከምኩበት ፍቅር ነው
ወይ እንዳልወቅሳት በድፍርት
ማስረጃ የለው የለሊት ቅዥት
♪
ሰው ያላርገው ወይ ያላሰበውን ተመሬት ተነስቶ
ይለፈልፋል ወይ በሰመመን እንቅልፍ በቅዠት ተሞልቶ
ባይኔ ምንም ነገር ጥፋት ሳላይባት ገና በምነ አልባት
የሌት ቅዠት ይዜ የምወዳትን ልጅ እንዴት ልፍረድባት
ለወሬ አይመች ወይ ለስሞታ
ሆኖ ባየልኝ ሰው በኔ ቦታ
ላልደረሰበት አይገረም ይሆናል
በራስ ሲሆን ግን ይከነክናል
ይሄን የቸገረ ነገረ እንቆቅልሽ ነገር
ፍረዱን ትቸዋለው ላገር
ምነው ይህንን ቅዠት የለሊት ቅዠትህ
አምላክ ባረገው ውሸትህ
♪
ለሊት አባኖኝ ቅዥትዋ
ጉዴን ሰማው ካንደበትዋ
የውን ታሪክ ነው ልብ ወለድ
የስዋ በኔ ላይ ሌላ ሰው መውደድ
እንዳልሰማ ሰው አላልፈው
የደከምኩበት ፍቅር ነው
ወይ እንዳልወቅሳት በድፍርት
ማስረጃ የለው የለሊት ቅዥት
♪
እስከዛሬ ደረስ ለስዋ የነበረኝ የፍቅር አመኔታ
በቅዠትዋ ምክኒያት አንዳንዴም ሲቋጠር አንዳንዴም ሲፈታ
ይሄን ሰሞንማ የልብዋን መሸፈት እያየው በህልሜ
የማጣት ቢመስለኝ እንደሰዋ መቃዥት ጀመርኩኝ በቁሜ
ስጋ ለባሽ ነኘ የሰው ፍጡር
ፍርድ አለብኝ ወይ ብጠረጥር
እንዲያ ሲያቃዥት ሆና ከጎኔ
ወይ ባልሰማዋት ምን ነበር ያኔ
ይሄን የቸገረ ነገረ እንቆቅልሽ ነገር
ፍረዱን ትቸዋለው ላገር
ምነው ይህንን ቅዠት የለሊት ቅዠትህ
አምላክ ባረገው ውሸትህ
አምላክ ባረገው ውሸትህ
አምላክ ባረገው ውሸትህ
አምላክ ባረገው ውሸትህ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri