ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ የመራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ የመራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
አመሉ ነው እና አመሉ ነውና ሳይጠሩት መምጣት
መሄዱ መልሶ ፍቅር ሳይነግሩት ምንም ሳይሉት
አመሉ ነው እና አመሉ ነውና ሳይጠሩት መምጣት
መሄዱ መልሶ ፍቅር ሳይነግሩት ምንም ሳይሉት
አንቺም ከሆንሽ በቃ የነሱ ዓይነት ቢጤ
በመሄድሽ አዝኖ ምን ቢቃጠል ውስጤ
በጭራሽ ሳልመስል ሰው ተራምዶ ያጣ
ስቄ እሸኝሻለው በውሸት በፈገግታ
ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ የመራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ የመራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ዛሬም ከኔ ሳታጭ ያን ንፁሕ መውደድ
ከጎኔ ለመራቅ ከጀመርሽ መንገድ
ስንለያይ ከፍቶኝ ምን ሆዴ ቢባባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በእምባ
እንደምንም ማዘን መከፋቴን መከፋቴን
አምቄው በውስጤ እምባዬን
ቅሬታ እንኳን ሳይታይ ፊቴ ላይ ፊቴ ላይ
ስሸኝሽ ይግረምሽ ስስቅ ስንለያይ
ዛሬም ከኔ ሳታጭ ያን ንፁሕ መውደድ
ከጎኔ ለመራቅ ከጀመርሽ መንገድ
ስንለያይ ከፍቶኝ ምን ሆዴ ቢባባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በእምባ
እንዳልሸኝሽ በእምባ እንዳልሸኝሽ በእምባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በእምባ
ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው
ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው
እንዳልሸኝሽ በእምባ እንዳልሸኝሽ በእምባ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri