Kishore Kumar Hits

Michael Belayneh - Ante Godana şarkı sözleri

Sanatçı: Michael Belayneh

albüm: Ante Godana ( Ethiopian Contemporary Music)


አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
ባላሰብኩት መንገድ እያመራ እግሬ
የት ቦታ አደረሰኝ ደግሞ ብሎ ዛሬ
ባልደከምኩ ነበረ በጉዞ አበሳ
ባውቀው መድረሻዬን ጥንቱን ሳልነሳ
እንደው ይጓዝ እንጂ የለት ስንቁን ይዞ
አንዴ ስለጻፈው ለዚች አለም ጉዞ
ንገረኝ ጎዳናው ስንቱ ተመለሰ
ስንቱ ካቀደበት ካሰበው ደረሰ
ስንቱ ካቀደበት ካሰበው ደረሰ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
አንገቴን ማስገቢያ ጎጆዬን ላቀና
ብዙ በመጓዜ በህይወት ጎዳና
ስወጣና ስወርድ ስሮጥ እንዳቅሜ
እኔ እንኳን ስንት አየሁ በዚች አጭር እድሜ
እኔ መች አሰብኩኝ ሲጀመር ጉዞዬ
አሁን ካለሁበት ያደርሰኛል ብዬ
አላዝንም በዛሬው በያዝኩት ጎዳና
በህይወት መንገድ ውስጥ ነገ አዲስ ነውና
ያላየሁት ነገ ሌላ ቀን ነውና
እኔ መች አሰብኩኝ ሲጀመር ጉዞዬ
አሁን ካለሁበት ያደርሰኛል ብዬ
አላዝንም በዛሬው በያዝኩት ጎዳና
በህይወት መንገድ ውስጥ ነገ አዲስ ነውና
እንደው ይጓዝ እንጂ የለት ስንቁን ይዞ
አንዴ ስለጻፈው ለዚች አለም ጉዞ
ንገረኝ ጎዳናው ስንቱ ተመለሰ
ስንቱ ካቀደበት ካሰበው ደረሰ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
አንተ ጎዳና አንተ መንገድ
ሰው እንዳይሄድ የለ እንዳይራመድ
አንተ ጎዳና

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar