Kishore Kumar Hits

Michael Belayneh - Lekas Lebego New şarkı sözleri

Sanatçı: Michael Belayneh

albüm: Ante Godana ( Ethiopian Contemporary Music)


በይቅርታ ታሽቶ ታክሞ በካሳ
የማይድን ህመም የማይሽር ጠባሳ
ልቤ ላይ ትታ መራቋ ከጎኔ
ለመርሳት ፍቅሯን ሆነልኝ ሰበቤ
እርሷን መርሻ ምክንያት አጥቼ ይሄኔ
የናፍቆቷ እስረኛ ሆኜ ነበር እኔ
ከራሴ በልጣ እሷን እንደመውደዴ
በውበት ቅርፃ እንደምን ማረጌ
ባይሆን የራቀች አስቀይማ ሆዴን
ይታየኝ ነበር የማጣት ማበዴን
ባልታሰበ ማ'በል ድንገት መመታቴ
ለካስ ለበጎ ነው ይንሁሉ ማየቴ

አይኔ አሁንማ ይቅር ይናፍቃት
ትዝ ብላው ድንገት ቢሞክር ባሳብ ሊስላት
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ
ያን በደሏን እስቲ ባፌ ልመርቀው
ኑርልኝ እድሜ ይስጥህ
ያክርምህ በልቤ ልበለው
ሆኖልኛልና ምክንያትህ ሰበብህ ሰበቤ
ፍቅር ትዝታዋን ለማውጣት ካሳቤ ከልቤ

በይቅርታ ታሽቶ ታክሞ በካሳ
የማይድን ህመም የማይሽር ጠባሳ
ልቤ ላይ ትታ መራቋ ከጎኔ
ለመርሳት ፍቅሯን ሆነልኝ ሰበቤ
ሃጢያቷ ቀስ በቀስ ቢሆንስ ምን ነበር
አይቼው ቢበዛ ቢፈፀም እያደር
ከራሴ በልጣ እሷን እንደመውደዴ
በውበት ቅርፇ እንደምን ማረጌ
ባይሆን የራቀች አስቀይማ ሆዴን
ይታየኝ ነበር የማጣት ማበዴን
ለካስ ልብ እንደሰው ደርሶ የሚርደው
የሚወስንበት አቶ ቢቃትት ነው

ያን በደሏን እስቲ ባፌ ልመርቀው
ኑርልኝ እድሜ ይስጥህ
ያክርምህ በልቤ ልበለው
ሆኖልኛልና ምክንያትህ ሰበብህ ሰበቤ
ፍቅር ትዝታዋን ለማውጣት ካሳቤ ከልቤ
አይኔ አሁንማ ይቅር ይናፍቃት
ትዝ ብላው ድንገት ቢሞክር ባሳብ ሊስላት
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar