ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ መራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
አመሉ ነው እና አመሉ ነውና ሳይጠሩት መምጣት
መሄዱ መልሶ ፍቅር ሳይነፍጉት ሂድም ሳይሉት
አንቺም ከሆንሽ በቃ የነሱ አይነት ቢጤ
በመሄድሽ አዝኖ ምን ቢቃጠል ውስጤ
በጭራሽ ሳልመስል ሰው ተላምዶ ያጣ
ስቄ እሸኝሻለው በውሸት በፈገግታ
ስቄ እሸኝሻለው ባዝንም የይስሙላ
ቀድመሽኝ መጥተሽ ከሄድሽ ወደ ሌላ
አሁን ከጀመርሽው ከኔ መራቅ ጉዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ሊያስቀርሽ ካልቻለ የኔ ፍቅር ይዞ
ዛሬም ከኔ ሳታጭ ያን ንፁህ መውደድ
ከጎኔ ለመራቅ ከጀመርሽ መንገድ
ስንለያይ ከፍቶኝ ምን ሆዴ ቢባባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በዕምባ
እንዳልሸኝሽ በዕምባ እንዳልሸኝሽ በዕምባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በዕምባ
ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው
ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው ስቄ እሸኝሻለው
እንዳልሸኝሽ በዕምባ እንዳልሸኝሽ በዕምባ
ስቄ እሸኝሻለው እንዳልሸኝሽ በዕምባ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri