Kishore Kumar Hits

Michael Belayneh - Afajeshign şarkı sözleri

Sanatçı: Michael Belayneh

albüm: Nafkot Ena Fikir


ሳላውቀው ቀርቼ ፈላጊሽ መብዛቱን
ስንቱ ሊማርክሽ ፈቅዶ መሰዋቱን
ብረዳማ ዛሬ ሁሉ እንደ ጎመጀ
መውደዴ ያልሰመረ መምጣትሽ አልበጀ
ወርቅ ሰም ሆኖብኝ ምን እንደምትሺ
ልክ እንደጭሰኛሽ ሁሉን ስልሽ እሺ
ሀሳቤ እንዳልገባሽ እንዳልተረዳሽኝ
ቁንጅና አስመክቶሽ ከስንቱ አፋጀሽኝ
ምኞትሽ ምንድነው አንቺ የሄዋን ቅጠል
በፍቅርሽ ነበልባል እያየሽ ስቃጠል
አርበኝነቱን ተይ
እምነቴን አትጣይ
አጥቼሽ እንዳልቀዝፍ ሰጋሁ ለመውደዴ
ይህ ልብሽ የያዘው ጫወታ ነው እንዴ
መልስ እንኳ አልሰጠሽኝ (ኡ አፋጀሽኝ)
ከስንቱ ነው ያፋጀሽኝ
ሳላውቀው ቀርቼ ፈላጊሽ መብዛቱን
ስንቱን ሊማርክሽ ፈቅዶ መሰዋቱን
ብረዳማ ዛሬ ሁሉ እንደጎመጀ
መውደዴ ያልሰመረ መምጣትሽ አልበጀ
ለካ ቆንጆ መውደድ አለው ብዙ ጣጣ
በምን ቀን አየሗት የሚያሰኝ ግን መጣ
ከምን ጣለኝ ዘንድሮ (ኡ አፋጀሽኝ)
አለ ልቤ ተቸግሮ
አንቺ ወዳጀ ብዙ መልሽ ተጠይቂ
ምነው ከሰው መሀል ሰው መውደድ አታውቂ
ሌላ የለም የሚሻል (ኡ አፋጀሽኝ)
ካንቺ መሆን ልቤ ይሻል
አፋጀሽኝ አፋጀሽኝ
ከስንቱ ሰው
ልቤ ሊተውሽ
አቅም ባነሰው
አፍጀሽኝ አፋጀሽኝ አፋጀሽኝ
አፋጀሽኝ (ኡ አፋጀሺኝ)
አፋጀሽኝ
(ኡ አፋጀሽኝ)

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar