ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ተናውጣለች ነፍሴ በእንግዳ ማእበል
ግን ሳለየው እንዴት አፈቀርኳት ልበል
በትር እንደቃጣች አልመክት በክንዴ
ለዛ ልብ ታጋይ ልረታ ነው እንዴ
ተፈጥራ እንጂ ይውደድሽ ተብላ
ስሜቴን ምን ለየው ከሌላ ከሌላ
መላመድ አልለው ገና በሳምንቱ
አይኖቿን መናፈቅ ምንድነው ምክንያቱ
ልወዳት ነው መሰለኝ
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
በቃል ያወደስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
በአይኔ የናፈኩት
ይመጣል ናፍቆቷ ላያስተኛኝ ምሎ
የልቤን መሳነፍ መራቅ ተከትሎ
ደጋግሞ ከአይኔ ላይ ምስሏ ይከሰታል
አብዝቼ ያሰብኩት ሰው እንደሷ የታል
ጉልበት ሰቷት እንጂ ልቤ እሷን ማለቱ
ምን ያቆነጃታል ታድያ በየለቱ
ልወዳት ካልሆነ ፍቅሯ ሊቆራኘኝ እሷን ብቻ ሚያሰኝ ምን ነገር አገኘኝ
ናፍቄ አልጠግብ ያቺን አደይ መሳይ
ደስ ይለኛል ደሞ ተገኝታ አይኖቿን ሳይ
ስሰነብት ሌት ቀን ሲቆጠር
ፍቅሯ ክንፍ አርጎኝ መታየቴ አይቀር
ልወዳት ነው መሰለኝ
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
ሳላውቅ ያመንኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
ሁሌ ያስታወስኩት
ልወዳት ነው መሰለኝ
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
ሳላውቅ ያመንኩት
ልወዳት ነው መሰል
ልቤን ጠረጠርኩት
እንደሷ ሰው የታል
ሁሌ ያስታወስኩት
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri