ቀዳሚ እዳልነበርኩ አንቺን ለመቅረቡ
ማማርሽ የገባኝ ዙርያሽ ሲያንዣብቡ
ያልተገለጠለት የቁንጅናሽ ቅኔ
ውበትሽ ያልጠራኝ ወዴት ነበር አይኔ
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ ሄድኩኝ ከጨረቃ ተሻግሬ
እኔ ሳይ ማዶ ውበት ነበር ቅርቤ ተጋርዶ
መሻት ተፅፎበት ፊታቸው ላይ ደምቆ
ለፍቅርሽ ቢማልል ሁሉም ሁሉን ንቆ
እልፍ ተመልካችሽ ላንቺ እንዳረገደ
ዳር አልባው ውበትሽ ገባኝ ከረፈደ
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ ሄድኩኝ ከጨረቃ ተሻግሬ
እኔ ሳይ ማዶ ውበት ነበር ቅርቤ ተጋርዶ
ያጠገቤ ትንግርት ተጋርዳኝ በቀትር
ያገር ያለህ እያልኩ አርቄ ስማትር
ማማርሽን ልብ ብል ባይናቸው አልፌ
አጀብሽ ቢበዛ አነቃኝ ከእንቅልፌ
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ ሄድኩኝ ከጨረቃ ተሻግሬ
እኔ ሳይ ማዶ ውበት ነበር ቅርቤ ተጋርዶ
ያጠገቤ ትንግርት ተጋርዳኝ በቀትር
ያገር ያለህ እያልኩ አርቄ ስማትር
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ ሄድኩኝ ከጨረቃ ተሻግሬ
እኔ ሳይ ማዶ ውበት ነበር ቅርቤ ተጋርዶ
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ (ኦሆሆሆ ኦሆሆሆ)
እኔ ሳይ ማዶ (ኦሆሆሆ ኦሆሆሆ)
ፀሀይ ሳለሽ ቅርቤ (ኦሆሆሆ ኦሆሆሆ)
እኔ ሳይ ማዶ (ኦሆሆሆ ኦሆሆሆ)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri