እሺ ብላኝ መጣሁ ሠመረልኝ ፍቅር
እውነቱን ብነግራት የመሸበት ላድር
እንዴትስ ደስ ይላል ወዶ መወደድ
ልቤ የፈቀዳት ልጅ መልሳ ስትፈቅድ
♪
ያደባባይ ሚስጥር ከሷ የተደበቀ
አፍኖኝ ሳጣጥር ሠርክ እያስጨነቀ
ልነግራት ስፎክር ደግሞ ሳመነታ
ስንት ጊዜ ሆነው ልቤ ከተረታ
እስከመቼ ፈርተህ ይውጣልህ ነግረሃት
ተብዬ ተልኬ በአጀባ ብርታት
እሺ ሆነ መልሷ መጣሁኝ በድል
የሞስራች ይዤ በደስታ ማእበል
እሺ ብላኝ መጣሁ ሠመረልኝ ፍቅር
እውነቱን ብነግራት የመሸበት ላድር
እንዴትስ ደስ ይላል ወዶ መወደድ
ልቤ የፈቀዳት ልጅ መልሳ ስትፈቅድ
♪
አንደበትም ለካ ደርሶ ይለግማል
ያሉትን ረስቶ ፈርቶ ይርበተበታል
እንዲህ እሺ ልትል በፍቅር ልካስ
ሠግቼ ነበረ ቃሉን መተንፈስ
♪
በእንቢታ ፍርሃት ታስሬ ከረምኩት
ተፈታሁ በፍቅር ስለተነፈስኩት
አረፈልኝ ልቤ ብያለሁ እፎይ
መታፈን ነው እዳ መናገር ሲሳይ
መታፈን ነው እዳ መናገር ሲሳይ
መታፈን ነው እዳ መናገር ሲሳይ
እሺ ብላኝ መጣሁ ሠመረልኝ ፍቅር
እውነቱን ብነግራት የመሸበት ላድር
እንዴትስ ደስ ይላል ወዶ መወደድ
ልቤ የፈቀዳት ልጅ መልሳ ስትፈቅድ
እሺ ብላኝ መጣሁ ሠመረልኝ ፍቅር
እውነቱን ብነግራት የመሸበት ላድር
እንዴትስ ደስ ይላል ወዶ መወደድ
ልቤ የፈቀዳት ልጅ መልሳ ስትፈቅድ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri