ወዶ ማግኝት ባይሆን እየወደዱ መኖር ሲቻል
ልቤ ምን አቅብጦት አንቺን በሀሳብ ይለያል
እንዳሻው እኔ ተስፋ አልጣ ብቻ
እሱ ነው ሁሉን ነገር መመለከቻ መመልከቻ
ቅን ካህን ያያት ነፍስሽ ለምለም
ሰው አንቺን ወዶ ሚያጣው የለም
ተወለድሽ በማሪያም ምህረት በፍቅር በውበት
በማር ሰራሽ ወይ ፈጣሪ ያ ጥበብ ቀማሪ
በማር ሰራሽ ወይ ባለ እጁ ያ ጥበብ በደጁ
የዝምታሽ ሞገስ ከሀምሌ ሰማይ ገዝፎ
እንቆቅልክ አለኝ ጥያቄውን ሁሉ አሰልፎ
የናፍቆትሽን ባህር እቀዝፋለሁ
እንጃ አንቺን እኔ በቃኝ መች እላለሁ
መች እላለሁ
ፍቅርሽ ነፍሴን የማጣት አልሻም መውደድሽን ማጣት
ፀጋ ነው መውደድ መወደድ በህይወት መንገድ
በማር ሰራሽ ወይ ፈጣሪ ያ ጥበብ ቀማሪ
በማር ሰራሽ ወይ ባለ እጁ ያ ጥበብ በደጁ
በማር ሰራሽ ወይ ፈጣሪ ያ ጥበብ ቀማሪ
በማር ሰራሽ ወይ ባለ እጁ ያ ጥበብ በደጁ
ልብሽ ምን እኔ ምን አውቃለሁ
እግርሽ ስር ስከተልሽ አለው
በማር ሰራሽ ወይ በማር ሰራሽ ወይ
በጥያቄ ብዙ ልቤን አላዝልም
ሳልወድሽ አልውልም አላድርም
በማር ሰራሽ ወይ
በማር ሰራሽ ወይ
በማር ሰራሽ ወይ ፈጣሪ ያ ጥበብ ቀማሪ
በማር ሰራሽ ወይ ባለ እጁ ያ ጥበብ በደጁ
በማር ሰራሽ ወይ ፈጣሪ ያ ጥበብ ቀማሪ
በማር ሰራሽ ወይ ባለ እጁ ያ ጥበብ በደጁ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri