አሸነፈ ልቤ ሸጋ ልጅ ወደደ
በፍቅር ሰከረ በደስታ አበደ
ክንፍ ያርገኝ ፍቅር ያንሳ ይጣለኝ
አንቺን መሳይ ወዶ ሰው ተከፍቶ አይገኝ
♪
ከሰው መሀል ምን አይኔ ላይ ጣለሽ
ላይመለስ ልቤ በቃ ተከተለሽ
እሰይምሽ እጠራሽ ቸገረኝ
ለቆንጆ የሚሆን ቆንጆ ቃል አጠረኝ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አይኖችሽን አይቼ ሳገግም
አንደበትሽ ይገለኛል ዳግም
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አይኖችሽን አይቼ ሳገግም
አንደበትሽ ይገለኛል ዳግም
♪
የስሜት ፈረቃ ፍቅርሽ ጥሎብኛል
ስትጠፊ ተክዤ ሳይሽ ደስ ይለኛል
ምን አይኔ ላይ ጣለሽ ልቤ እንዲደነግጥ
አንቺን የመሰለ አላየሁም በእርግጥ
♪
ራሴን አልሞግት ለምን ሆነ ብዬ
ብዙ እሄዳለሁ ልቤን ተከትዬ
አላጠፋሽ እኔምም አልበደልኩኝ
ተወዳጅ ልጅ ታየኝ ወዳጅ ልጅ ወደድኩኝ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አይኖችሽን አይቼ ሳገግም
አንደበትሽ ይገለኛል ዳግም
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
አይኖችሽን አይቼ ሳገግም
አንደበትሽ ይገለኛል ዳግም
♪
አሸነፈ ልቤ ሸጋ ልጅ ወደደ
በፍቅር ሰከረ በደስታ አበደ
(አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ)
አፍቅሬሽ አፍቅሬሻለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri