Kishore Kumar Hits

Neway Debebe - Ayaya şarkı sözleri

Sanatçı: Neway Debebe

albüm: Best of Neway Debebe Collection


ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ
ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ
ሰንዝሮ እማይመልስ ወርዶ እማይረታ
በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ
እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና
የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና
ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወዲያ ማዶ
የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ (አቤት)
ልክ እንደጀግና ሰው ምንኛ በረታሁ
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (ምንኛ በረታሁ ምንኛ በረታሁ)
ጎጃም ተሻግሬ ጎበዝ ሆኜ መጣሁ
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (ጀግና ሆኜ መጣሁ አንቺን ይዤ መጣሁ)
እንግዲያው ያውልሽ ውሰጂኝ ማርኪና
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (ውሰጂኝ ማርኪና ውሰጂኝ ማርኪና)
እንደፈለግሽ አርጊኝ የበላይ ነሽና
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (የበላይ ነሽና የጎበዝ ነሽና)
ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ
አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማርዋ
ጋምዬ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ
ደፋር አርጊው ልቤን እንደ በላይዬ
ጋምዬ ጋሜዋ ወይ ደምዬ ውው ደሜዋ
እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
እመይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
ሁል ጊዜ ከፍ ብለሽ የምትቀመጪ
የበላይ ሁነሽ ነው የምትመረጪ
በላይ የመረቀው ሀገሩን ነው መሰል
ቢወለድ ጀግና ሰው የሚያስጠራ በድል
የበላይን ፀባይ ይዘዋል ሰዎቹም
ለፍቅር ነው እንጂ ለፀብ አይመቹም
ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ
ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ
ሰንዝሮ እማይመልስ ወርዶ እማይረታ
በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ
እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና
የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና
ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወዲያ ማዶ
የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ
ዙሪያ ዳር ድንበሩን አገሩን ኩሩበት
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (አገሩን ኩሩበት አገሩን ኩሩበት)
እነበላይ ናቸው የተወለዱበት
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (የተፈጠሩበት ታሪክ የሰሩበት)
ከእንግዲህ ጎጃም ላይ ምን ተሰራ አትበሉ
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (ምን ተሰራ አትበሉ ምን ተሰራ አትበሉ)
ታሪክ ጠይቃችሁ በላይ በላይ በሉ
ሆይ ሆይ ሆይ ሆይ (ጀግናው በላይ በሉ ጎበዝ ወዳድ ሁሉ)
ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ
አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማሬዋ
ጋምዬ ነይ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ
ደፋር አርጊው ልቤን እንደበላይዬ
ጋምዬ ጋሜዋ ጋምዬ ጋሜዋ
እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
እመይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ
ሀይማኖተ ፅኑ ልበ ኩሩ ነሽ
ከነበላይ ሀገር ጎጃም ተወልደሽ
እረርዬ ንዬ እረንዬው መላ
ጎጃም ተገበየ ፍቅርና ተድላ
እኚህ ጎጃሜዎች ልዩ ጣእም አላቸው
የንቦች እንጀራ ማር እያበላቸው
አቤት ምቺ
አቤት ምቺ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar