ሱፍ ገበርዲን ለብሰህ ናልኝ አልልህም
የዘመኑን ካፖርት ደርብ አልልህም
ያገሬን የወንዜን እጀጠባቡን
የሚያምረኝ ኩታ ነው የቤት ፈትሉን
ያማረው እንዝርቴ የፈተለልህን
ጠባቡ ቀሰሜ የፈጠረልህን
ና ልደርብልህ ሽሙንሙን ኩታህን
ና ልደርብልህ ሽሙንሙን ኩታህን
አሸወይና ሸወይና ወይንዬ
አሸወይና ውበት ፀዳል ሸግዬ
አሸወይና ሽወይና ወይናው
አሸወይና ናና ሸሞናው
አሸወይና ሽሙንሙን ብለህ
አሸወይና አበባ አጣጥለህ
አሸወይና ከወጣበት ቦታ
አሸወይና እንገናኝ ማታ
በድብቅ ጨዋታ አንጀት ማራሱን
ላስተምርህ አስተምረኝ ሆዴ አጨራረሱን
እኔብስ እኔብስ ብለን ጀምረነው
ቀድሞ ሚጥለውን ደፋሩን ባየነው
የማሳው ጉያ ነው ፍቅር ማፍለቂያችን
የግራሩ ጥላ የፎይታ ጣዛችን
የለመለመው መስክ መተቃቀፊያችን
እዚያው ነው እዚያው ነው መቀጣጠሪያችን
ያማረው እንዝርቴ የፈተለልህን
ጠባቡ ቀሰሜ የፈጠረልህን
ና ልደርብልህ ሽሙንሙን ኩታህን
ና ልደርብልህ ሽሙንሙን ኩታህን
አሸወይና ሸወይና ወይንዬ
አሸወይና ውበት ፀዳል ሸግዬ
አሸወይና ሽወይና ወይናው
አሸወይና ናና ሸሞናው
አሸወይና ሽሙንሙን ብለህ
አሸወይና አበባ አጣጥለህ
አሸወይና ከወጣበት ቦታ
አሸወይና እንገናኝ ማታ
በድብቅ ጨዋታ አንጀት ማራሱን
ላስተምርህ አስተምረኝ ሆዴ አጨራረሱን
እኔብስ እኔብስ ብለን ጀምረነው
ቀድሞ ሚጥለውን ደፋሩን ባየነው
ቀድሞ ሚጥለውን ደፋሩን ባየነው
ቀድሞ ሚጥለውን ደፋሩን ባየነው
በድብቅ ጨዋታ አንጀት ማራሱን
ላስተምርህ አስተምረኝ ሆዴ አጨራረሱን
እኔብስ እኔብስ ብለን ጀምረነው
ቀድሞ ሚጥለውን ደፋሩን ባየነው
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri