ምንድነው መጨነቅ በሆነው ባልሆነው
10 ሞልቶ አያቅም አለም ዘጠኝ ነው
በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ
በጨዋታ መሃል ፍቅርን መደብለቅ ነው
ነገርም ሲመጣ ደጅን ማሳየት ነው
በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ
ሱፉን ግጥም አርጎ ተከርክሞ ፀጉሩን
መልዓክ መስሎ ታየኝ ሃያል ነው ማማሩ
ወዬው ጉድ፣ወዬው ጉድ፣ ወዬው ጉድ
ወደድኩሽ አለና ጠላሁሽ ቢለኝ
እኔስ መስሎኝ ነበር ሌላ ማይገኝ
ወዬው ጉድ፣ወዬው ጉድ፣ ወዬው ጉድ
እሞታለሁ ለፍቅር አድራለሁኝ ሜዳ
እበራለሁ ለፍቅር ነይ ሲለኝ ማለዳ
ማለዳ፣ ማለዳ
ዘመኑ ምን አለኝ ዘመኑ ወርቅ ነው
ፍቅር ያለቀ እለት ጉዴ ነው ጉዴ ነው
ጉዴ ነው፣ ጉዴ ነው
አትሸበር ልቤ በሆነው ባልሆነው
ስለ ሰው ስለ ሰው ቀድጄ ልልበሰው
እንዲህ አደለም ወይ የነገር ምላሹ
ሲወዱት ያጠፋል አመለ ትኑሹ
ለቅዱስ ዮሃንስ ይጠጣ አደል ጠላ
እኔም በተራዬ ሰው ወድጄ ልጥላ
አለሁ አለሁ ሲለኝ መቸም እያለሁ
ጣል ጣል ሲያረገኝ ደሞ እቀርበዋለሁ
ደሞ እቀርበዋለሁ፤ ደሞ እቀርበዋለሁ
ጨዋታ መልካም ነው ቢከፋም
እንጫወት ዛሬ እድሜ ሞልቶ አይተርፍም
በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ
እረ እናንተ ሆዬ ፍቅር አይገልም ገሎ
ባይሆን ሂዱ ይላል ክዳንን አስጥሎ
በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ፣ በሉ እንጅ
አንድ ጉዳይኝ የማማክራችሁ
ፍቅር የጠፋ ለት ያመኛል ባካችሁ
ወዬው ጉድ፣ወዬው ጉድ፣ ወዬው ጉድ
በኔ እንዳይጀመር በፍቅር ሰው ሲሞት
እኔው በገዛ እጄ ልብ ልቤን አጣሁት
ወዬው ጉድ፣ወዬው ጉድ፣ ወዬው ጉድ
እሞታለሁ ለፍቅር አድራለሁኝ ሜዳ
እበራለሁ ለፍቅር ነይ ሲለኝ ማለዳ
ማለዳ፣ ማለዳ
ዘመኑ ምን አለኝ ዘመኑ ወርቅ ነው
ፍቅር ያለቀ እለት ጉዴ ነው ጉዴ ነው
ጉዴ ነው፣ ጉዴ ነው
አትሸበር ልቤ በሆነው ባልሆነው
ስለ ሰው ስለ ሰው ቀድጄ ልልበሰው
እንዲህ አደለም ወይ የነገር መሸላሹ
ሲወዱት ያጠፋል አመለ ትኑሹ
ለቅዱስ ዮሃንስ ይጠጣ አደል ጠላ
እኔም በተራዬ ሰው ወድጄ ልጥላ
አለሁ አለሁ ሲለኝ መቸም እያለሁ
ጣል ጤፋል ሲያረገኝ ደሞ እቀርበዋለሁ
ደሞ እቀርበዋለሁ፤ ደሞ እቀርበዋለሁ
ደሞ እቀርበዋለሁ
ደሞ እቀርበዋለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri