ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ፣ ኑሮ መልከ ብዙ
ሲያዎጣና ሲያዎርድ ብዙ ነው መዘዙ
ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ
ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ
ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ፣ ኑሮ ትኒሹ
ሀብታም ደሃ ሳትል ሁሉን አስለቃሹ
ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ
ወይ ኑሮ፣ ወይ ኑሮ
አራዳ ወጥቼ ሸንብራ ገዝች
"ተመስገን" እላለሁ ጠርጥሬ በልቼ
አደርኩኝ ሌሊቱን እንቅልፌን አጥቼ
ማወራረጃዬ ውሃን ረስቼ
ኣኣኣኣ ውሃን ረስቼ
ተሰርቼ ወጣሁ ወደ ሰው መንደር
አይደላ አይጎረብጥ የፈረንጆች አገር
ከሃገሩ የወጣ ከሃገሩ እስኪመለስ
ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ
ፈረስ ፈረስ ፈረስ ፈረስ
ፈረስ ፈረስ ፈረስ ፈረስ
አንድ ሰው ነበረ ሁሌ እምያሳስቀኝ
ስዎጣ ስገባ ወይንሸት የሚለኝ
ወይንሸት፣ ወይንዬ፣ ወይና፣ ወይና
ይሄን መንገደኛ ዘንድሮስ ናፈቅኩት
ባገኘሁትና ወይኑ ብዬ ባልኩት
ወይኑ፣ ወይንዬ፣ ወይና፣ ወይና
ወይኒ ብሎ ጠርቶ ስም የረወጣልኝን
ሄጄ ፈልጋለሁ ይገኝ እንደሆን
አላገኘሁትም የልቤን ወዳጅ
ስለሱ ሳወጋ እኖራለሁ እንጅ
ሃገሬ ወጥቼ ኑሮን ሳሳድደው
ብቻዬን ቀረሁ ትዳርን ሳልይዘው
አላውቅበት ብዬ መንከባከቡን
ጌታዬ የምትለው አገኘህ ይሆን
ጌታ፣ ጌታዬ፣ ጌታ፣ ጌታ
ጌቱ፣ ጌታዬ፣ ጌታ፣ ጌታ
ጌታዬ የምትለው አገኘህ ይሆን
ጌታዬ የምትለው አገኘህ ይሆን
ቀረሁኝ ብቻዬን ትዳርን ሳልይዘው
ብቻዬን ቀረሁ ትዳርን ሳልይዘው
ጌጌጌጌጌ ጌታዬ የምትለው አገኘህ ይሆን
ጌጌጌጌጌ ጌታዬ የምትለው አገኘህ ይሆን
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri