Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Emyae şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Fikir


ምንኛ ችግር ነው እናት መሆንሽ
ከመጸነስ ጀምሮ እስከመውለድሽ
አቤት እማምዬ አንቺ ጭንቀትሽ
እማምዬ እናቴ እንዴት ላርግልሽ
ዘጠኝ ወራት በሙሉ ችለሽ በሆድሽ
በምጥ እና በጣር እንደዛ ወልደሽ
ሶስት አመት በእቅፍሽ በወገብ አዝለሽ
ከማር የሚጣፍጥ ጡትሽን አጥብተሽ
እሁ እምዬ ኡሁ እናቴ(2) እናቴ
ባለቀሰ ቁጥር ህጻኑ ልጅሽ እኔን እኔን ብለሽ አብረሽ አልቅሰሽ(2)
እንዲ በመከራ ልጅ አሳደገሽ
እንዴት ይመለሳል ከባድ ውለታሽ(2)
እምዬ (4)ደስ ይበልሽ
ዛሬ (4)ደረስኩልሽ
እምዬ(4)ምን ልታዘዝሽ
ዛሬ (4)ሳለሽ በቁምሽ
ምንኛ ችግር ነው እናት መሆንሽ
ከመጸነስ ጀምሮ እስከመውለድሽ
አቤት እማምዬ አንቺ ጭንቀትሽ
እማምዬ እናቴ እንዴት ላርግልሽ
ደግሞ በዚሁ ላይ የስራሽ መብዛቱ
እንጀራ መገገሩ ወፍጮ ማስፈጨቱ
ውሃውን ከወንዙ በእንስራ መቅዳቱ
ተቆጥሮ አያልቅም ስራው ከማጀቱ
እሁ እምዬ ኡሁ እናቴ(2) እናቴ
ባለቀሰ ቁጥር ህጻኑ ልጅሽ እኔን እኔን ብለሽ አብረሽ አልቅሰሽ(2)
እንዲ በመከራ ልጅ አሳደገሽ
እንዴት ይመለሳል ከባድ ውለታሽ(2)
እምዬ (4)ደስ ይበልሽ
ዛሬ (4)ደረስኩልሽ
እምዬ(4)ምን ልታዘዝሽ
ዛሬ (4)ሳለሽ በቁምሽ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar