ወገኔ ትልቁ ሲያከብረኝ ደሀው
አይኔ በፈሰሰው በሆንኩት ውሀው
እንደጥላ ወዶ በየትም የሚታይ
አድኖኛል ጌታ የፍቅር ተከታይ
አድኖኛል ጌታ የፍቅር ተከታይ
እስትንፋሴን ይውሰድ
ነብሴም ትሁን ነብሱ
እድሜ ጤናም የለኝ አልኖርም ታለርሱ
እድሜ ጤናም የለኝ አልኖርም ታለርሱ
ከሙዚቃ ምርኮ ፣ መላቀቄም ይቅር
ታስሬ ኖራለሁ በወገኔ ፍቅር
ታስሬ ኖራለሁ በወገኔ ፍቅር
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
የ የ ተከፋን ሁሉ
በምን አይቼ
አ አ አ አንጎራጉራለሁ ከዚሁ ተነስቼ
የስንቱን ውለታ ችዬ ልመልሰው
የብዙዎች ብድር አይወጣም በአንድ ሰው
ተድላ ብቻ አይደለም ይዞ ሚያዘፍነኝ
ሁሉም ይሰማኛል እኔም የሁሉ ነኝ
ቢመጣም መለየት ደርሶ ሚበትን
የሚወደኝ ሁሉ ልቡ የኔ ቤት ነው
የሚወደኝ ሁሉ ልቡ የኔ ቤት ነው
የሰው መውደድ አለው ያሻውን ያደርጋል
በዚህ አለም ለሁሉም ፍቅር ያስፈልጋል
በዚህ አለም ለሁሉም ፍቅር ያስፈልጋል
ለእስካሁኑ ፍቅር አመሰግናለሁ
ለዛሬ እንዲህ ብልም ለነገም እዚህ አለሁ
ለዛሬ እንዲህ ብልም ለነገም እዚህ አለሁ አለሁ
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
(አረ ወየው ወየው ወየው ወየው)
የስንቱን ውለታ ችዬ ልመልሰው
የብዙዎች ብድር አይወጣም በአንድ ሰው
እንዴት ልናገረው የሆዴን ነገሬ
በሰው ፍቅር ታስሮ የሰራ አካሌ
በሰው ፍቅር ታስሮ የሰራ አካሌ
ምን ይንቀኝ ብዬ ክቤ የምጥረው
በሰው ልብ አደል ወይ ሁሌ የምኖረው
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri