ወዲያ ማዶ እያየሁ የቅርቡን አርቄ
ምነው እኖራለው የሄደን ናፍቄ
የዓይኖቼ ዳርቻ ዕንባ እያቀረረ
ብዙ ትውስታውን እኔ ላይ የቀረ
የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር
ያሳለፍነው እንዴት ይቅር
ታስሬአለሁ በናፍቆትህ
ሌቱን ቀኑን በቅዠትህ
ትውስታዬ የኔ ወዳጅ
ያ ፍቅራችን ይታወስ እንጅ
ይታወስ እንጅ
ወደኃላ ሄዶ እየተመለሰ
ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ
ይኸው ደግሞ መሸ አይኔ ሊንከራተት
መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት
የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር
ያሳለፍነው እንዴት ይቅር
ወይ ከንቱነት ምስኪንነት
ይችን ፍቅር ላልመልሳት
ከምወደው ተለይቼ
እኖራለሁ ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
ወደኃላ ሄዶ እየተመለስ
ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ
ይኸው ደግሞ መሸ አይኔ ሊንከራተት
መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት
ወይ ከንቱነት ምስኪንነት
ይችን ፍቅር ላልመልሳት
ከምወደው ተለይቼ
እኖራለሁ ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri