አዬ ሰው
አዬ ሰው መሞት አነሰው
እምነቴን አፈራረሰው
ቃሉን አምኜ ስወደው
ክደትን ምን አስመረጠው
(አዬ ሰው) (አዬ ሰው)
የእውነት አምላክ ሲያሳየኝ
ፊትለፊት ሲያገጣጥመኝ
አይኑን ከአይኔ ላይ መለሰው
አይቶ እንዳላየ አዬ ሰው
አዬ ሰው አዬ ሰው አዬ ሰው (ሰው)
ትላለች ቀበሮ ለሰው ሞት አነሰው (ሰው)
አየሁት ወዳጄን እጇን በእጁ ይዞ (ሰው)
ማመን ቢቸግረኝ አይኔ ቀረ ፈዞ (ሰው)
ያነባል ያነባል ያነባል ያነባል አይኔ እንባ ተሞልቶ
የተማመንኩበት ያፈቀርኩት ወዳጅ ሳየው ቃሉን በልቶ
ልሂደው ልሂደው ልሂደው ልጓዘው ልሂደው ልሂደው እስከመጨረሻው
ሲያምኑት የሚታመን የሰው ልጅ መኖሪያው የት ይሆን አድራሻው
አይ ድካሜ ሞኝነቴ ከሰው እምነት መመኘቴ
ጉድ ብዬ ብለየው የሚመጣው ያው ሰው ነው
አዬ ሰው
አዬ ሰው መሞት አነሰው
እምነቴን አፈራረሰው
ቃሉን አምኜ ስወደው
ክደትን ምን አስመረጠው
አዬ ሰው የእውነት አምላክ ሲያሳየኝ
ፊትለፊት ሲያገጣጥመኝ
አይኑን ከአይኔ ላይ መለሰው
አይቶ እንዳላየ አዬ ሰው
እኔ ፍቅር ይዞኝ ገና በዋዜማው (ሰው)
ሰው ቢሆን ነው እንጂ በሌላ የታማው (ሰው)
ከእንግዲህ የእኔ ልብ መቼም ሰው አያምንም (ሰው)
መፍራት መጠርጠር ነው ይሄንም ያንንም ያንንም (ሰው)
ያነባል ያነባል ያነባል ያነባል አይኔ እንባ ተሞልቶ
የተማመንኩበት ያፈቀርኩት ወዳጅ ሳየው ቃሉን በልቶ
ልሂደው ልሂደው ልሂደው ልሂደው ልሂደው ልጓዘው እስከመጨረሻው
ሲያምኑት የሚታመን የሰው ልጅ መኖሪያው የት ይሆን አድራሻው
መጀመሪያ ሲፈጥረው ክፉ እና ደግ አለው ሰው
ከሰው ፍፁም ባይገኝም ደግ ሰው ግን አይነሳኝም
መጀመሪያ ሲፈጥረው ክፉ እና ደግ አለው ሰው
ከሰው ፍፁም ባይገኝም ደግ ሰው ግን አይነሳኝም
መጀመሪያ ሲፈጥረው ክፉ እና ደግ አለው ሰው
ከሰው ፍፁም ባይገኝም ደግ ሰው ግን አይነሳኝም
መጀመሪያ ሲፈጥረው ክፉ እና ደግ አለው ሰው
ከሰው ፍፁም ባይገኝም ደግ ሰው ግን አይነሳኝም
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri