በጠራዉ ሰማይ ላይ ጭር ባለዉ ለሊት
ቁጭ ብዬ እንደዘበት ታየኝ የአንቺ ዉበት
ኮከቦች አጥረዉሽ ብልጭ ድርግም ሲሉ
አይ የለሊቱ ግርማ የዉበትሽ ፀዳሉ
የለሊቱ ግርማ የዉበትሽ ፀዳሉ
♪
ቁጭ ብዬ አየሁት በረንዳዬ ላይ
ጨረቃ ጨረቃ ዉበትሽ እንደዚህ ነዉ ወይ
ቁጭ ብዬ አየሁት በረንዳዬ ላይ
ጨረቃ ዉበትሽ እንደዚህ ነዉ ወይ
♪
ጸጥ ባለዉ ለሊት ዉበትሽ ናፍቆት
የሰዉ ልጅ መጠቀ አንቺን ለማየት
መርምሮ ሊረዳ ምስጥርሽን ሊያደንቅ
እንደ መሬት ሁሉ በአንቺም ሊራቀቅ
አይ እንደ መሬት ሁሉ በአንቺም ሊራቀቅ
♪
ጨረቃ ዉበትሽ ደግሞ ብርሃንሽ
ልዩ ነዉ ተፈጥሮሽ አጢኖ ላየሽ
ብርሃንሽ ዉበት ነዉ ዉብ ነዉ ብርሃንሽ
ጨረቃ በስሜት አትኩሮ ላየሽ
♪
በጠራዉ ሰማይ ላይ ጭር ባለዉ ለሊት
ቁጭ ብዬ እንደዘበት ታየኝ የአንቺ ዉበት
ኮከቦች አጥረዉሽ ብልጭ ድርግም ሲሉ
የለሊቱ ግርማ የዉበትሽ ፀዳሉ
የለሊቱ ግርማ የዉበትሽ ፀዳሉ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri