ጸጉርሽ ሃር ይመስላል አሆዬ
ብለህ አታድንቀኝ አሆዬ
አንድ ቀን ይረግፋል አሆዬ
ለጊዜዉ ቢያምርብኝ አሆዬ
ለጊዜዉ ቢያምርብኝ አሆዬ
ጉንጭሽ ብርቱካን ነዉ አሆዬ
ብለህ አትደልለኝ አሆዬ
እየሟሟ ይሄዳል አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
አሀሀይ ከእዉነተኛ ስሜት ዉደደኝ ዉደደኝ
አሀሀይ በቁምነገር በሀቅ አፍቅረኝ አፍቅረኝ
አሀሀይ መልኬን አታድንቀዉ አሆዬ ይቅርብኝ ይቅርብኝ
አሀሀይ መልኬን አታድንቀዉ አሆዬ ይቅርብኝ ይቅርብኝ
ሽንጤን አታድንቀዉ አሆዬ
እርሳዉ እርሳዉ አሆዬ
ጥርሴን አትዉደድ አሆዬ
ተወዉ ተወዉ አሆዬ
ተወዉ ተወዉ አሆዬ
ጸባይ ቁምነገሬን አሆዬ
አተኩር አተኩር አሆዬ
መልክ ረጋፊ ነዉ አሆዬ
ይቅር ይቅር አሆዬ
ይቅር ይቅር አሆዬ
አሀሀይ በዉበት ምርጫ ላይ ዋሆሆይ ማተኮር ማተኮር
አሀሀይ መሰረት አይሆንም አሆዬ ለፍቅር ለፍቅር
አሀሀይ እዉነት ከወደድከኝ አሆሆይ ፍፁም ከልብህ
አሀሀይ ምርጫህ ይስተካካል ዋሆዬ ይቅር ማሾፍህ
ጸጉርሽ ሃር ይመስላል አሆዬ
ብለህ አታድንቀኝ አሆዬ
አንድ ቀን ይረግፋል አሆዬ
ለጊዜዉ ቢያምርብኝ አሆዬ
ለጊዜዉ ቢያምርብኝ አሆዬ
ጉንጭሽ ብርቱካን ነዉ አሆዬ
ብለህ አትደልለኝ አሆዬ
እየሟሟ ይሄዳል አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እየሟሟ ይሄዳል አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆዬ
እርጅና ሲጫነኝ አሆ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri