እህህህ አይቼ ላፍቅረህ
እህህህ ሰምቼ ልቅረብህ
አለሜ ምኑ ተነካና
መቼ ተለማመድኩና
አሀሀ ይቀረኛል ገና
አይገፋም ወዳጅ ሚስጥር ያካፈሉት
ሚስጥር ያካፈሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
እንደምን እንደምን እንደምን ሊረሱት
ከፈረስ ይቀድማን ሲያካልል ዙሪያውን
ሲያካልል ዙሪያውን
አቆራርጦ ጋራ ሰንጥቆ ሜዳውን
አቆራርጦ ጋራ ሰንጥቆ ሜዳውን
ከሶ መግባባትን ያውቃል ጥበብን
የወዳጅ አያያዝ አቀራረቡን
አትመጥነው በሉት ያምራል ፈገግታው
አትቆጥበው በሉት ይሁን ጨዋታው
እንደተቸረ ከሩቅ የሚመጣ
አጋጣሚ አይደለ ስቆ የሚረታው
እስኪ ሰከን በልተው አታስቸኩለኝ
ገና በውጥኑ ልሞት ነው አትበለኝ
ፍቅር አይለካም ገና በጅምሩ
ካከራረሙ ነው መጣፈጥ መምረሩ
ኦሆይ ኦሆይ ኦሆይ ኦሆይ
አንጀት ተደልሎ በቁራሽ ቢከርምም
ገላ ተሸንግሎ በነጠላ ቢያድርም
አከላት በወረት ቢደሰት በለቱ
ማግስቱን ይመጣል መሰለቻቸቱ
ኦሆይ አሄይ ኦሆይ አሄይ
መሰለቻቸቱ
እህህህ አይቼ ላፍቅረህ
እህህህ ሰምቼ ልቅረብህ
አለሜ ምኑ ተነካና
መቼ ተለማመድኩና
አሀሀ ይቀረኛል ገና
አይገፋም ወዳጅ ምስጥር ያካፈሉት
ምስጥር ያካፈሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
ፍቅር ተጎራርሰው ተጋርተው የበሉት
እንደምን እንደምን እንደምን ረሱት
ከፈረስ ይቀድማን ሲያካልል ዙሪያውን
ሲያካልል ዙሪያውን
አቆራርጦ ጋራ ሰንጥቆ ሜዳውን
አቆራርጦ ጋራ ሰንጥቆ ሜዳውን
አቀበት ቁልቁለቱን ሸንተረር ወንዙን
የወዳጅ አያያዝ አቀራረቡን
አትመጥነው በሉት ያምራል ፈገግታው
አትቆጥበው በሉት ይሁን ጨዋታው
እንደተቸረ ከሩቅ የሚመጣ
አጋጣሚ አይደለ ስቆ የሚረታው
የዘለቄታሽ ነኝ አትበለኝ ፈጥነህ
አባብለኝ አባብለኝ ከልቤ እስከማምንህ
ስወድህ ውደደኝ ስቀርብህ ቅረበኝ
መሃላ እያበዛህ በአፍህ አትደልለኝ
ኦሆይ ኦሆይ
በጥቅሻ አመልህ ስንቱን አባብለሃል
በአይኖችህ ንግግር ከእጅህ አግብተአል
ጎሽመህ ጎሻሽመህ የተላመድካቸው
የተኙት ሴሰኞች ኧረ እነማን ናቸው
ኦሆይ ኦሄይ ኦሆይ ኦሄይ
አለው ዘዴ አለው እንጂ ሚስጥር
ብልህ የሚያታልል አፍዝዞ የሚያስቀር
አማለለኝ እና ሄድኩኝ ተከትዬው
ያካላቱ ማማር ተስተካክሎ ባየው
ኦሆይ አሄይ
እንደው በዚህ ገላ ፍቅር ጨምሮበት
ያየው አደነቀው ልቡን ገበረለት
ለካስ አለ ገላ ከአደይ የደመቀ
ለካስ አለው ውበት የተፍለቀለቀ
ኦሆይ አሄይ ኦሆይ አሄይ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri