ብዙነህ አሉ፣ ብዙነህ አሉ
ስንት ያየሁብህ ህመሜ
እንክትክት እያለ ስሜ
ወድጄህ በሌለኝ አቅሜ
እስቲ ልበልህ ብዙ አለሜ
(ብዙ አለሜ) ታምቼ፣ ታምቼ ስሜ ባገር ጠፍቶ
ሲሆን መተረቻ
ሆኖ ሲውል የሰው መዛበቻ
(ብዙ አለሜ) ከሰው ያሳደረኝ የሌለበት አቻ
(ብዙ አለሜ) ችሎ ማለፍ ብቻ
(ብዙ አለሜ) እተክዝ ነበረ ጭንቀቴ እየጸና
እየበዛብኝ
ብቸኝነት እየከበበኝ
(ብዙ አለሜ) ይኸው ያንተ ፍቅር እያጠበልኝ
(ብዙ አለሜ) ካሳብ ተሻለኝ
ሲነካኩኝ ባንተው ነገር
አልፋለሁ ሳልናገር
ሰው ስለሰው ወግ ይወዳል
መታማት መች ይጎዳል
አካሌ ቢጎዳ ቢጸና ህመሜ
ለኔስ ሀኪሜ
ብዙ አለሜ
ስወድህ የለኝ ወደር
የለኝ ወደር
ልቤ ላይ ልስጥህ መንደር
መንፈሴም አብሮህ ይደር፣ ይደር
አካሌም አብሮህ ይደር፣ ይደር
ብዙነህ አሉ፣ ብዙነህ አሉ
ስንት ያየሁብህ ህመሜ
እንክትክት እያለ ስሜ
ወድጄህ በሌለኝ አቅሜ
እስቲ ልበልህ ብዙ አለሜ
(ብዙ አለሜ) ብበላም ብጠጣም ባምር ብለባብስ
ሀሳብ ባይነካኝ
ለብቻዬ ሀብቱ ቢተርፈኝ
(ብዙ አለሜ) ሲያከንፍ ያልቃል እንጂ ሲያብከነክነኝ
(ብዙ አለሜ) ፍሬም ሳይሆነኝ
(ብዙ አለሜ) ጉልቻ ደርድሬ ጭራሮ ለቅሜ
ማምጣቱን ብወድም
አያይዤ መሞቁን ብለምድም
(ብዙ አለሜ) አንድ እንጨት ቢለኮስ ቢጫር ቢማገድም
(ብዙ አለሜ) ብቻውን አይነድም
የኔው አካል ሰውነቴ
አንተ ነህ ቀሪ ሀብቴ
ሀሜት ቀሎ ከገለባ
ያዝልቅህ አንተ አበባ
አካሌ ቢጎዳ ቢጸና ህመሜ
ለኔስ ሀኪሜ
ብዙ አለሜ
ስወድህ የለኝ ወደር
የለኝ ወደር
ልቤ ላይ ልስጥህ መንደር
መንፈሴም አብሮህ ይደር፣ ይደር
አካሌም አብሮህ ይደር፣ ይደር
ብዙነህ አሉ፣ ብዙነህ አሉ
ስንት ያየሁብህ ህመሜ
እንክትክት እያለ ስሜ
ወድጄህ በሌለኝ አቅሜ
እስቲ ልበልህ ብዙ አለሜ
እስቲ ልበልህ ብዙ አለሜ
እስቲ ልበልህ ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
ብዙ አለሜ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri