Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Musica şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Musica


ከሰማይ ሰማያት
አድማስን አስሰሽ
ፅንፍ ከዋክብትን
ጨረቃን አዳርሰሽ አዳርሰሽ
ምድርን በውብ ቋንቋ
በመንፈስ ያደሽው
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም
ፍቅርን ያለበሽው ያለበሽው
ዓለም ሲያሸበርቅ ህይወትን አፍክቶ
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ
እንደ ሰማይ ፈክቶ
የሰላም ነፀብራቅ
ፀዳል የወረሳት
ባንቺ ነው ሙዚቃ አድማስ የታደሰው
ባንቺ ነው ሙዚቃ አድማስ የታደሰው
ከሰማይ ሰማያት
አድማስን አስሰሽ
ፅንፍ ከዋክብትን
ጨረቃን አዳርሰሽ አዳርሰሽ
ምድርን በውብ ቋንቋ
በመንፈስ ያደሽው
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም
ፍቅርን ያለበሽው ያለበሽው
የሰው ልጅ በፍቅር
ወይ በሀዘን ሲመታ
ኑሮውን በሚዛን
ሲፈትሽ ሲለካ
ሲከፋው ሲደሰት
ሲማከር ከልቡ
ሙዚቃ ብቻ ነሽ ስንቅና ቀለቡ
ሙዚቃ ብቻ ነሽ ስንቅና ቀለቡ
ከሰማይ ሰማያት
አድማስን አስሰሽ
ፅንፍ ከዋክብትን
ጨረቃን አዳርሰሽ አዳርሰሽ
ምድርን በውብ ቋንቋ
በመንፈስ ያደሽው
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም
ፍቅርን ያለበሽው ያለበሽው

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar