በቀን አስር ግዜ በደጅህ ማለፌን
ለሊት መንቃቴን ሳልጨርስ እንቅልፌን
ስምክን ደጋግሜ ሳነሳው መዋሌን
ይምጣ ወዳጅ ዘመድ ይቀበለኝ ቃሌን
ልቤጥሎኝ ሄደ አንተ ቤት ማደሩን
ገና በሩቅ ሳይህ ሆዴ መሸበሩን
ሞት ካለየኝ በቀር አንተን እንደማልተው
እንደው ይሄን ነገር ለማን ሰው ላጫውተው
በቀን አስር ግዜ በደጅህ ማለፌን
ለሊት መንቃቴን ሳልጨርስ እንቅልፌን
ስምክን ደጋግሜ ሳነሳው መዋሌን
ይምጣ ወዳጅ ዘመድ ይቀበለኝ ቃሌን
አሁንም አሁንም አንተን ቢያነሱልኝ
በጨዋታ መሃል ስምህን ቢጠሩልኝ
ውበትህን አድንቀው በመልካም ሲያነሱህ
መስማት ደስ ይለኛል አንተን ሲያወድሱህ
በቀን አስር ግዜ በደጅህ ማለፌን
ለሊት መንቃቴን ሳልጨርስ እንቅልፌን
ስምህን ደጋግሜ ሳነሳው መዋሌን
ይምጣ ወዳጅ ዘመድ ይቀበለኝ ቃሌን
ከሁሉም መውደድህ እንደሚብስብኝ
ከማንም ከምንም እንደምትበልጥብኝ
ላንተ እንደምጨነቅ ከሁሉ አስበልጬ
ምንም ሳልደብቅህ ልንገርህ ገልጬ
ምንም ሳልደብቅህ ልንገርህ ገልጬ
በቀን አስር ግዜ በደጅህ ማለፌን
ለሊት መንቃቴን ሳልጨርስ እንቅልፌን
ስምህን ደጋግሜ ሳነሳው መዋሌን
ይምጣ ወዳጅ ዘመድ ይቀበለኝ ቃሌን...
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri