ወዳንተ ስልከው አማላጁን ሁሉ አማላጁን ሁሉ
ከደጃፍሕ ደርሶ ይመለሳል አሉ ይመለሳል አሉ
ካንተ ሚያስታርቀኝ ሁነኛ ወዳጅህ ሁነኛ ወዳጅህ
እንዴት ያለ ሰው ነው የሚቆም ከደጅህ የሚቆም ከደጅህ
እችለው ይመስል ላንዳፍታ ስትርቀኝ
ጧት አኮርፍሀለው ማታ ልትናፍቀኝ
ዳግም ላላኮርፍህ ምዬ ተገዝቼ
በማን ልታረቅ ማንን ዋስ ጠርቼ
ወዳንተ ስልከው አማላጁን ሁሉ አማላጁን ሁሉ
ከደጃፍሕ ደርሶ ይመለሳል አሉ ይመለሳል አሉ
ካንተ ሚያስታርቀኝ ሁነኛ ወዳጅህ ሁነኛ ወዳጅህ
እንዴት ያለ ሰው ነው የሚቆም ከደጅህ የሚቆም ከደጅህ
የትኛው ዘመድ ነው አንተን የሚረታ
እስቲ ቢያማልደኝ ልላከው ላንዳአፍታ
የልቤን መናፈቅ ያይኔን መንከራተት
ይቅር ትለኝ ነበር ዐይንህ ቢመለከት
ወዳንተ ስልከው አማላጁን ሁሉ አማላጁን ሁሉ
ከደጃፍሕ ደርሶ ይመለሳል አሉ ይመለሳል አሉ
ካንተ ሚያስታርቀኝ ሁነኛ ወዳጅህ ሁነኛ ወዳጅህ
እንዴት ያለ ሰው ነው የሚቆም ከደጅህ የሚቆም ከደጅህ
ምነው እንዲህ አርጎ ልብህ ደነደነ
ይቅር በለኝ ስለው በእኔ ላይ ጨከነ
ቂም የሚያሲዝ ነው ወይ አሁን የኔ ጉዳይ
ይታረቅ የለም ወይ ሰው ካባቱ ገዳይ
ወዳንተ ስልከው አማላጁን ሁሉ አማላጁን ሁሉ
ከደጃፍሕ ደርሶ ይመለሳል አሉ ይመለሳል አሉ
ካንተ ሚያስታርቀኝ ሁነኛ ወዳጅህ ሁነኛ ወዳጅህ
እንዴት ያለ ሰው ነው የሚቆም ከደጅህ
የሚቆም ከደጅህ የሚቆም ከደጅህ
የሚቆም ከደጅህ የሚቆም ከደጅህ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri