Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Yeserge Tistaw şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Sebebu


እንዲያ ተሞሽሬ አምሮብኝ ተውቤ
አማረብሽ ሲሉኝ መላው ቤተሰቤ
ዛሬም በዐይን በዐይኔ ይመጣል ትዝታው
እንዴት እንደነበረ የሰርጌ ሁኔታው
አይዞሽ ሙሽሪት አይበልሽ ቅር አይበልሽ ቅር
ትዳር ጥሩ ነው ያሞቃል ፍቅር ያሞቃል ፍቅር
አይዞሽ ሙሽሪት አይልሽ ከፋ አይልሽ ከፋ
ሁሉም ያገባል በየወረፋ በየወረፋ
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
ሎጋው ሽቦ እያለ ሲገባ ሰርገኛ
አናስገባም ብሎ ሲጨፍር ቤተኛ
እጄን በእጁ አልፎ ሲያወጣኝ ሙሽራው
ልዩ ስሜት አለኝ ዛሬ እንኳን ሳወራው
እስቲ ብቅ በይ አንዴ ልይሽ አንዴ ልይሽ
የኛ ሙሽራ የኛ ያሉሽ የኛ ያሉሽ
በየት አድርጌ በየት ልይሽ በየት ልይሽ
ወርቁን ጋርደውሽ ዘመዶችሽ ዘመዶችሽ
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
ምንድነው ዝምታው ሚዜው ጨፍር እንጂ
ሰተንህ የለም ወይ ይችን መሳይ ልጅ
ብለው ዘፈኑበት ይቺን? አንወድም
ያለበለዚያማ ልጃችን አትሄድም
እሰይ አበጀሽ አንቺ የኛ ልጅ አንቺ የኛ ልጅ
በስለት ተገኘሽ በሺ አማላጅ በሺ አማላጅ
የኛ ሙሽራ የቆንጆ ቆንጆ የቆንጆ ቆንጆ
እንግዲህ ይስጥሽ የሞቀ ጎጆ የሞቀ ጎጆ
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
እየተባለ የተዘፈነው ሰርጌ ትዝታው
ዛሬም ህያው ነው
ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው
ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው
ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው
ሰርጌ ትዝታው ዛሬም ህያው ነው...

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar