Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Libe Teshagere şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Sebebu


አላስቀምጥ ቢለኝ ያገር ልጅ በናፍቆት
ልቤ ተሻገረ ባህሩን ሰንጥቆት
ትውስ አለኝና ካገር ልጅ ጨዋታ
ኩልል አለ እምባዬ ሆኖ መንታ መንታ
ሆ' ሆኖ መንታ መንታ
ባህሩን በዋና አካሌ ምድሩን በባዶ እግሩ ምድሩን በባዶ እግሩ
ልቤ እሱን ፍለጋ ሄዷል ወደገሩ ሄዷል ወደገሩ
እንዲያው ለጨዋታ ሰው አይጠፋም እንጂ ሰው አይጠፋም እንጂ
ማን እንደወንዜ ልጅ እንዳገሬ ልጅ እንዳገሬ ልጅ
ቢከፋ አይዞሽ የሚል ቢታመሙ ደራሽ
ወዳጅ እንደ አገር ልጅ አልተገኘም ጭራሽ
ዐይንህን ለማየት እኔ እንዲህ ስቸኩል
እንደምን ይዞሀል ፍቅር ባንተ በኩል
ናናናናናና ናንዬ እንደምነህ
ናናናናና ነው... ነው ናናናናናና
አላስቀምጥ ቢለኝ ያገር ልጅ በናፍቆት
ልቤ ተሻገረ ባህሩን ሰንጥቆት
ትውስ አለኝና ካገር ልጅ ጨዋታ
ኩልል አለ እምባዬ ሆኖ መንታ መንታ
ሆ' ሆኖ መንታ መንታ
የሰው ባህል አይደል አላየው ሰርቄ አላየው ሰርቄ
ወይ ከተፍ አላልኩኝ ያለሁት እርቄ ያለሁት እርቄ
አልጠራው ወጥቼ ባይኔ አላባብለው ባይኔ አላባብለው
እንደው በምን ዘዴ ናፍቆቱን ልቻለው ናፍቆቱን ልቻለው
ቢከፋ አይዞሽ የሚል ቢታመሙ ደራሽ
ወዳጅ እንደ ሀገር ልጅ አልተገኘም ጭራሽ
ዐይንህን ለማየት እኔ እንዲህ ስቸኩል
እንደምን ይዞሀል ፍቅር ባንተ በኩል
ናናናናናና ናንዬ እንደምነህ
ናናናናና ነው... ነው ናናናናናና
አላስቀምጥ ቢለኝ ያገር ልጅ በናፍቆት
ልቤ ተሻገረ ባህሩን ሰንጥቆት
ትውስ አለኝና ካገር ልጅ ጨዋታ
ኩልል አለ እምባዬ ሆኖ መንታ መንታ
ሆ' ሆኖ መንታ መንታ
አይሰማ ድምፄን ብቆም ከተራራው ብቆም ከተራራው
ቶሎ ድርስ ብዬ ልጁን እንዳልጠራው ልጁን እንዳልጠራው
እዚህ ካለሁበት እጅግ መናፈቄን እጅግ መናፈቄን
ሂድ ተሻገር ልቤ ንገርልኝ ጭንቄን ንገርልኝ ጭንቄን
ቢከፋ አይዞሽ የሚል ቢታመሙ ደራሽ
ወዳጅ እንደ ሀገር ልጅ አልተገኘም ጭራሽ
ዐይንህን ለማየት እኔ እንዲህ ስቸኩል
እንደምን ይዞሀል ፍቅር ባንተ በኩል
ናናናናናና ናንዬ እንደምነህ
ናናናናና ነው... ነው ናናናናናና...

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar