Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Lib Weled şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Ćhewa


ሀሁን አቦጊዳን ወንጌልን ተምሬ
የዕውቀትን ብርሃን ካየሁኝ ጀምሬ
ባህሪውን ሁሉ ጽፌ ያልጨረስኩት
አለኝ የህልም ወዳጅ በሃሳብ ያሰፈርኩት
በሃሳብ ያሰፈርኩት

ለብቻዬ ማየው ይሄ የልቤ ድርሰት
ይሄ የልቤ ድርሰት
ምነው እውን ሆኖ በገሃድ ቢከሰት
በገሃድ ቢከሰት
ምንነበር ፈጣሪ ነፍስ እየለገሠው
ባካል ቢያመጣልኝ ይሄንን የህልም ሰው
እንደ ዕድል ነው ዕጣ
ለሰው ሰው ሲወጣ
የምኞት ድርሰቴ
ያሻኛል ለህይወቴ
በመጣልኝ ቤቴ

እኔ እንደ ፈጣሪ አልሰራም ሕይወት
እንደው ምኞት እንጂ በሃሳብ መጫወት
ትንፋሹን ዘርቶበት ሥጋ ያለበሰው
ልቤ የጀመረውን አምላክ በጨረሰው
አምላክ በጨረሰው

በፍለጋ ተስፋ ከሃሳቤ ሳልወጣ
ከሃሳቤ ሳልወጣ
ቢገጥመኝ እያሉ ሁሌ የሚያልሙትን
ሁሌ የሚያልሙትን
ልብ የወለደውን ከምን ያገኙታል
ከምን ያገኙታል
ባይሆን ካጋጣሚ ከእድል ይመኙታል

እንደ ዕድል ነው እንደ ዕጣ
ለሰውም ሰው ሲወጣ
ይህ የምኞት ድርሰቴ
ያሻኛል ለህይወቴ
በመጣልኝ ቤቴ
በመጣልኝ ቤቴ
በመጣልኝ ቤቴ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar