ይሄን መከዳዬን እስቲ ልንተራሰው
ያንተ ፍቅር መቶ አንጀቴን ካራሰው
ደጋግሞ ደጋግሞ ይለኛል ደስ ደስ
እየው በመምጣትህ ህይወቴ ሲታደስ
እፎይ እፎይ እፎይ
እፎይ ተገላገልኩ
እፎይ እፎይ እፎይ እፎይይይ
አረፍኩኝ ካሳቤ
መልሶ አመጣልኝ አንተን አንተን አንተን
አንተን ካጠገቤ አንተን አንተን አንተን
አንተን ካጠገቤ
ሰላሜ ሲበዛ እልል በይ ይለኛል
እልል እልል እልል እልልልል
እልል በይ ይለኛል
እንዲህ ያለ ደስታ
እንዲህ ያለ ደስታ
አሁን ከየት ይገኛል
አሁን አሁን አሁን
አሁን ከየት ይገኛል
ወዳጅሽ የት ጠፋ ብለው ሲጠይቁኝ
ምንም አይረዱት እንደሚያስጨንቁኝ
እፎይታን ሳጣጥም ተደሰተች ነፍሴ
ጓዙን ይዞ ገባ ሰላም ከመንፈሴ
መቼም የፈጣሪ አያልቅም ምህረቱ
ተገኘ መሰለኝ ዘንድሮስ ካንጀቱ
አውጣኝ አውጣኝ
ብየው ነበር ጌታን ከጭንቀቴ
ይኸው በጄ ገባ ባካል ሰውነቴ
እፎይ እፎይ እፎይ
እፎይ ተገላገልኩ
እፎይ እፎይ እፎይ እፎይይይ
አረፍኩኝ ካሳቤ
መልሶ አመጣልኝ አንተን አንተን አንተን
አንተን ካጠገቤ አንተን አንተን አንተን
አንተን ካጠገቤ
ሰላሜ ሲበዛ እልል በይ ይለኛል
እልል እልል እልል እልልልል
እልል በይ ይለኛል
እንዲህ ያለ ደስታ
እንዲህ ያለ ደስታ
አሁን ከየት ይገኛል
አሁን አሁን አሁን
አሁን ከየት ይገኛል
ብዙ ቀናት ኖሯል ጭር ካለ ደጄ
ሌላም ወገን የለኝ አንተው ነህ ወዳጄ
ምኞቴ ነበረ ቀድሞም ባትለየኝ
ይመስገን አምላኬ አይንህን አሳየኝ
ይመስገን አምላኬ አይንህን አሳየኝ
አይንህን አሳየኝ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri