Kishore Kumar Hits

Aster Aweke - Tiwsta şarkı sözleri

Sanatçı: Aster Aweke

albüm: Ćhewa


ወዲያ ማዶ እያየሁ የቅርቡን አርቄ
ምነው እኖራለው የሄደ ናፍቄ
የዓይኖቼ ዳርቻ እንባ እያቀረረ
ብዙ ትውስታ አለ ከኔ አልርቅ ያለ

የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር
ያሳለፍነው እንዴት ይቅር

ታስሬያለው በናፍቆትህ
ሌትም ቀኑን በቅዠትህ
ትውስታዬ የኔ ወዳጅ
ያ ፍቅራችን ይታወስ እንጂ
ይታወስ እንጂ

ወደ ኋላ ሄዶ እየተመለሰ
ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ
ይሄው ደግሞ መሸ ዓይኔ ሊንከራተት
መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት

የኔ ወዳጅ የኔ ፍቅር

ያሳለፍነው እንዴት ይቅር

ወይ ከንቱነት ምስኪንነት
ያቺን ፍቅር ላልመልሳት
ከምወደው ተለይቼ
እኖራለው ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ

ወደ ኋላ ሄዶ እየተመለሰ
ናፍቆት ፍቅር ሲጭር እሳት የለበሰ
ይሄው ደግሞ መሸ ዓይኔ ሊንከራተት
መንፈሴ ሊረበሽ ልቤ ሊርበተበት

ወይ ከንቱነት ምስኪንነት
ያቺን ፍቅር ላልመልሳት
ከምወደው ተለይቼ
እኖራለው ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ
ደስታን አጥቼ

ደስታን አጥቼ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar