የፍቅርን ረድዔት አብዝቶ
የሰላምን ፀሐይ አብርቶ
ደስታና ፍቅር
እርቅ ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
በአንድነት በሰላም አሽብርቆ
ይምጣልን በእልልታ ታርቆ ደምቆ
እልልል እልልታ
ፍቅር ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
በምስራቅ በምዕራብ በደቡብ ሠሜን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
በሁሉም ማዕዘን እርቅ ይውረድልን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
ኢትዮጵያ ይላታል ሲጠራ እናቱን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
ሃገር ያለ ፍቅር የማይሆነውን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
እንመኝ መልካሙን ደስ ደስ ይበለን
ተመስገን እንበለው ለዚህ ላደረስን
በፍቅር በደስታ እጅ ለእጅ ተያይዘን
ይቅር እንባባል ስለ እናታችን
በአንድነት በደስታ እናቴ ትድመቅ
በይቅር ይቅርታ ቤታችን ይሙቅ
አንድ ነሽ እናቴ የምስራቅ ጮራይቱ
የሀይማኖት ደብር የታሪክ ምድሪቱ
ኢትዮጵያይቱ
ኢትዮጵያዬ
ኢትዮጵያይቱ
ምድሪቱ
የፍቅርን ረድዔት አብዝቶ
የሰላምን ፀሃይ አብርቶ
ደስታና ፍቅር እርቅ ይሁንልን
በኢትዮጵያችን
በአንድነት በሰላም አሽብርቆ
ይምጣልን በእልልታ ታርቆ ደምቆ
እልልል እልልታ
ፍቅር ይውረድልን
በኢትዮጵያችን
ሁሉም በየእምነቱ የሚኖርብሽ
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
እምዬ እናታችን የሁላችን ነሽ
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
አባት ያቆዩልንን አንድነታችንን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
ለትውልድ እናቆይ ኢትዮጵያችንን
(ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ)
መፋቀር ትርጉም ነው የአንድነት ሚስጥር
የማስተዋል ብቃት የትውልድን ክብር
ደጋ ወይናደጋው ቆላው መሬታችን
የገደል የምንጩ ፈውስ ነው ውሃችን
በአንድነት በደስታ እናቴ ትድመቅ
በይቅር ይቅርታ ቤታችን ይሙቅ
አንድ ነሽ እናቴ የምስራቅ ጮራይቱ
የሃይማኖት ደብር የታሪክ ምድሪቱ
ኢትዮጵያይቱ
ኢትዮጵያዬ
ኢትዮጵያይቱ
ምድሪቱ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
ኢትዮጵያዬ
እማማዬ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri