እንዲህ አርገን ስራውን ሁሉ አምነን
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን
ነገር ግን ዳግም ይምጣል ስላልን
ከፃድቃንም ከመላእክትም ቢሆን
የሚያውቅ የለም የሚመጣበት ቀኑን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓት
ግርድ ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ከያለበት ይሰበሰባል አንድ አፍታ
አጥንታችን ትቢያ የሆነው አፈር
ጅብ የበላው የተበተነው ከዱር
የራስ ጠጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር
ተሳስቶ የአንዱን ወደ አንዱ ሳይዞር
በየራሱ ይሰበሰባል ሁሉም
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም
ነብስ የሌለው በድን ይሆናል ፍፁም
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ይነሳሉ መልካም የሰሩ በእልልታ
የብርሃናት የብርሃን ቀሚስ ለብሰው
እንደ ፀሀይ እንደ ጨረቃ ደምቀው
እግዚአብሔርን ፈጣሪያቸውን መስለው
ይሰሙና በቀኙ ቆመው ፍርዱን
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር
ተግቦ ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር
ገብቶ መውጣት አጊኝቶ ማጣት ችጋር
የሌለባት ደገኛይቱን ሀገር
ይወርሳሉ መልካም የሰሩ በምድር
ሀጥያንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው
መልካቸውም እጅግ ከቁራ ጠቁረው
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው
ዲያብሎስን አለቃቸውን መስለው
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው
ከለቅሶና ጥርስ ማፏጨት በቀር
ተድላ ደስታ የሌለባትን ሀገር
ይወርሳሉ ክፉ የሰሩ በምድር
እንዲህ አርገው መፅሀፍት ሁሉ እንዳሉን
በየስራው ይከፍለዋል ሁሉን
ስብሀት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ለአለም እስከ ዘለዓለም ድረስ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri