Kishore Kumar Hits

Alemu Aga - Medinanna zelesegna şarkı sözleri

Sanatçı: Alemu Aga

albüm: Ethiopiques, Vol. 11: Bèguèna (The Harp of King David)


ወንድሜ ጠፍቶኝ ስሄድ ነብር አግኝቶኝ ከመንገድ
አልተመለስኩም ወድያው ሄድኩ እኔን ይብላኝ እያልኩ
አልተመለስኩም ወድያው ሄድኩ እኔን ይብላኝ እያልኩ
የቀድሞ ዘመን ስህተት በፆም ቀን አሳ መብላት
የአሁን ዘመን ሰው አያውቅ መላ በልቶም ሽሮ ነው ሚበላ
የአሁን ዘመን ሰው አያውቅ መላ በልቶም ሽሮ ነው ሚበላ
የኛ መድኃኒት አይነቶች በብዙ አሉ ቅመሞች
ነገር ግን እኔ ሳስበው ስራስሩ መልካም ነው
ነገር ግን እኔ ሳስበው ስራስሩ መልካም ነው
ያባቶቻችን ውሃ ዋና ላይ ላዩን ነበር በጤና
የዛሬ ልጆች ይበልጣሉ ወስጥ ለውስጥ ይሄዳሉ
የዛሬ ልጆች ይበልጣሉ ወስጥ ለውስጥ ይሄዳሉ
ኮሶ ተጣብቶኝ ትላንትና መድኃኒት ስሻን ዋልኩና
ድንገት ሰማሁኝ አንድ ዜና የወዲያ ሰዎች ህግ ደንብ አይከለክልም ምግብ
የኛስ ስርዓት ከባድ እንዲያው በባዶ ሆድ
የኛስ ስርዓት ከባድ እንዲያው በባዶ ሆድ
የጌታችንን ፀባይ ያለኔ የሚያውቅ አለ ወይ
ማታ ለግብር መልካም ሰው ቀን ሲቆጣክ ክፉ ሰው
ማታ ለግብር መልካም ሰው ቀን ሲቆጣክ ክፉ ሰው
አያሳስትም ሰዓትን ቀጠሮ ያከብራል ሞት
ሽማግሌ አይል ህፃን ሞት ጠያቂ ነው ሁሉን
አሁን ይመጣል በእውነት ሞት ብሎ አይቀር ሞት
አሁን ይመጣል በእውነት ሞት ብሎ አይቀር ሞት
እሁድ ቅዳሜን ቢሆን እበላ ነበር ምሳዬን
እንዲህ በጦም ቀን የምዞረው ለጊዜ ማድረሻ ነው
እንዲህ በጦም ቀን የምዞረው ለጊዜ ማድረሻ ነው
ትንሽ ቤት ሰራሁ እንደአቅመኛ ሁለት ሶስት ሰው የምታስተኛ
አላስገባ አለች እሷው ጠባ ሰው በሰው ላይ እየገባ
አላስገባ አለች እሷው ጠባ ሰው በሰው ላይ እየገባ
ከታች ጉርጓዱ የጠለቀ ከላይ ጉበኑን የጠበቀ
እንዲህም አርገው ሚሰሩት መፍረሱ አይቀርም ቤት
እንዲህም አርገው ሚሰሩት መፍረሱ አይቀርም ቤት
የዛሬ ዘመን ሰው ስራ ሳሩም ቅጠሉም አያኮራ
እውቀቱስ ያንተ መሰለኝ በአብነት አድነኝ
እውቀቱስ ያንተ መሰለኝ በአብነት አድነኝ
አባቶቻችን ካህናት ሲጠመጥሙ ከጥንት
ለስልጣናቸው ለክህነት መለያ ነበር ምልክት
አሁንማ ጠምጣሞቹ ሹሞቹና ጠበቆቹ
አሁንማ ጠምጣሞቹ ሹሞቹና ጠበቆቹ
ይህች በቅሎዬ ምን ሆነች አጉል መጥፎ አመል ለመደች
የጎረቤቷን እያየች ጭነት መገልበት አመጣች
የጎረቤቷን እያየች ጭነት መገልበት አመጣች
የሰሞኑ ጋብቻ ድንቅነቱ ከቀድሞ እጅጉን መለየቱ
መሆኑ ቀርቶ እስከሞት ተጀመረ ተጧሪ ፈቶ እንታት ማግባት
መሆኑ ቀርቶ እስከሞት ተጀመረ ተጧሪ ፈቶ እንታት ማግባት

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar