Kishore Kumar Hits

Alemu Aga - Abatatchen hoy şarkı sözleri

Sanatçı: Alemu Aga

albüm: Ethiopiques, Vol. 11: Bèguèna (The Harp of King David)


አባታችን በሰማዮች ላይ ያለህ
ተለይቶ ይመስገን ክቡር ስምህ
መንግስትህን የምንፈልጋት ከጥንቱ
በልጅነት ትምጣ ትሰጠን አቤቱ
ፍቃድህም ይህ እንዲደረግ ይሁን
በሰማይም ሞተን ተነስተን ከደይን
እንድንኖር ምስጋናህ ምግብ ሆኖን
ዛሬም በምድር በስጋ ህይወት ሳለን
ምግባችንን በየዕለቱ አውቀህ ስጠን
ይቅር በለን የበደልንህም ቢኖር
ወንድማችን የበደለንን ነገር
እንደ አቅማችን እኛም እንድንል ይቅር
በገሀነብ ከክፉ ሁሉ መዓት
አትጣለን አድነን እንጂ ከሞት
ይቺን መንግስት የማያገኛት ህልፈት
ጌትነትም ከሀዲነትም ክብርም
ናቸውና ያንተ ገንዘቦች ሁሉም
ለአለም ለአለሙ አለም አሜን
የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ከጌታ
ሰላም ለኪ ብሎ በሰጠሽ ሰላምታ
እኔ ባርያሽ ልብሴን ስታጠቅ ስፈታ
ሰላም ልልሽ ይገባኛል ጠዋት ማታ
ማርያም ሆይ እመቤቴ ሆይ ድንግል
እዳለሽ ቅዱስ ገብርኤል ሰላም
ሰላም ለኪ እንደ እርሱ ሁሉ እኔም
የጠፋልሽ የነፍስ ስጋ መርገም
ብሩክ ነው የማህፀንሽ ፍሬም
እንደቀድሞው ብሩክ አምላክ ነው ዛሬም
እግዚአብሔር ወልድ በመጣህ ጊዜ ለካሳ
እንበለዘር እንደ ንብ እና አሳ
ከነብስሽ ነብስ ከስጋሽ ስጋ ቢነሳ
ደስ ያለሽ ሆይ ፀጋን አጊኝተሽ ከጌታ
ደስ ይበልሽ በማቀርብልሽ ሰላምታ
ለምኚልን ሳትሰለቺ ጠዋት ማታ
ውድ ልጅሽ እንዲያደርግልን ይቅርታ
ይቅር ብሎ ሀጥያታችንን ሁሉን
እንዲያድነን ባንቺ ተማፅነን አለን

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar