ነይይይ ኧረ ነይይይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
በአምባሰል በባቲ በአንቺሁዬ ለኔ
በትዝታ መንገድ አንቺ ትመጪ እኔ
አላርፍ ያለው ልቤ አምባሰል ሄደና
ተፈውሶ መጣ በትዝታ ቃና
ፎቶዬን አይቼው የልጅነቴን
ደግሞም በመስተዋት አይቼው መልኬን
ግሩም ሆኖ ቀረ የዘመኑ ሳቄ
ስለዋወጥ ቆጨኝ ወይ አለማወቄ
ወይ አለማወቄ
እትቱ በረደኝ ብርድ ይሞቃል ወይ
የማያውቁት ሀገር ይናፍቃል ወይ
አንቺ እንደምን አለሽ እኔስ እንደምንም
ሆድ ይቻለው እንጂ የማልሰማው የለም
እቱ የእናቴ ልጅ አይምሰልሽ ከቶ
አይምሮም ይሸሻል ከሰው ተቆራኝቶ
ዝም ብለሽ ታዘቢ ያንቺም ቀን ይመጣል
ትዕግስት አብሮሽ ይደር ሁሉም ነገር ያልፋል
ሁሉም ነገር ያልፋል
ጊዜ እየለወጠው ለዛና ቁመና
እስኪ አንቺው ፍረጂኝ ፎቶዬን እዪና
ራሴን በራሴ አየሁት እኔን
የልጅነት ቅርሴን ያውም ፎቶዬን
እመስል የነበረ አዕምሮ ጠንካራ
ለካስ ለዚህ ኖሯል ያ ሁሉ ፉከራ
አይዞሽ የእናቴ ልጅ ሁሉም ነገር ያልፋል
ጊዜም እንደዘበት ከ'ድሜ ጋራ ያዘግማል
ከ'ድሜ ጋራ ያዘግማል
ነይይይ ኧረ ነይይይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ኧረ ነይ ኧረ ነይ
ታሪኬ በአለም ላይ ይወሳ ነበረ
መብቴን በማስከበር እታወቅ ነበረ
ውበቴ አሸብርቆ እታይ የነበረ
ዛሬስ መጨረሻው ስደት ሆኖ ቀረ
እማዋይሽ ማነሽ ተመልከች የስስቱን
የዘመን ኪሳራ ሰው ሆኖ መቅረቱን
ጠይም ጉንጭ አኩራፊ ያን እንክብል ዓይኔን
ፎቶዬን እዪና ተመልከቺኝ እኔን
ተመልከቺኝ እኔን
መልኬን በመስተዋት ሳላየው ቀርቼ
እኔን የሚመስል ሌላ ቅርስ አይቼ
ለብዙ ዘመናት አድናቆት ነበረኝ
ዛሬስ መጨረሻው ፎቶዬ ነገረኝ
ፎቶዬን አይቼው የልጅነቴን
ደግሞም በመስተዋት አይቼው መልኬን
ግሩም ሆኖ ቀረ የዘመኑ ሳቄ
ስለዋወጥ ቆጨኝ ወይ አለማወቄ
ወይ አለማወቄ ወይ አለማወቄ
ወይ አለማወቄ ወይ አለማወቄ
ወይ አለማወቄ ወይ አለማወቄ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri