ሳይላዎስ አፏ - ቃልም ሳይዎጣው
ይናገራል አይኗ - ፍቅርን በቋንቋው
ሳይላዎስ አፏ - ቃልም ሳይዎጣው
ይናገራል አይኗ - ፍቅርን በቋንቋው
ፍላጎት ከሆዷ (ከሆዷ): ታምቆ ቢውልም (ቢውልም)
ከፍቅሯ አገኛለሁ: ካይኗ ላይ ሁሉንም
የኔንም ሰዋሰዉ (ሰዋሰዉ): የውስጥ ቅኔ (የኔን)
አዋቂው አይኗ ነው የፍላጎቴን
ከፍጥረት አድሎ (አድሎ) ያስተውላል ጠልቆ (ጠልቆ)
ስያሜ ያጣው አይኗ: ከጠቢብ አልቆ
ጠበቃ ሳያቆም (ሳያቆም): በስውር ችሎት (አሃሃ)
ያሳምናል አይኗ: ከርቱዕ አንደበት
እንቅልፍም መሽቶ ባይጨፍናቸው
አልሰለች እስኪነጋ ባያቸው
ጠብቀው ድንበር ከለላውን
ያይኗን ዘብ ያንን ሽፋሽፍቱን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
ሳይላዎስ አፏ - ቃልም ሳይዎጣው
ይናገራል አይኗ - ፍቅርን በቋንቋው
ሳይላዎስ አፏ - ቃልም ሳይዎጣው
ይናገራል አይኗ - ፍቅርን በቋንቋው
ሁሉም እንደራሱ (የራሱ): ቢኖር ስያሜው (ዋው)
የራሱ ቋንቋ አለው የሷ ለብችው
ነገርን ደብቆ (ደብቆ): አይውል በዘበት (አሃሃ)
ሁሉን ይፈታዋል: በራሱ ስሌት
ኮኮብ አይመስለው (መስለው): የንጋት አብሳሪ (አሃሃ)
ጦረኛ ነው አይኗ: መንፈስ አሸባሪ
ምንም ቃል ባይወጣው (ባይወጣው) አፏ ባይተነፍስ (አሃሃ)
አንጀት አርስ አይኗ: ይዘምራል የነብስ
ጦረኛውን ያንን ሞገደኛውን
ለሚያዝን ልብ የሚረታውን
ፈቅጄ ሰጥቻለሁ እጄን
ከልለው ከክፉ ያን አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
እንቅልፍም መሽቶ ባይጨፍናቸው
አልሰለች እስኪነጋ ባያቸው
ጠብቀው ድንበር ከለላውን
ያይኗን ዘብ ያንን ሽፋሽፍቱን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
አሃሃሃ አይኗን አሃሃሃ አይኗን
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri