መለኛ ነሽ አሉ መቼም መላ አይገድሽ
እስኪ ስጪኝ መላ አትሸሽጊኝ እባክሽ
መቼም መለኛ ነሽ እስኪ ጀባ በይኝ
እቴ ከማክዳሽ ከእልፍኝሽ አውይኝ
♪
ደብቄ እንደያዝኩሽ አምቄ በውስጤ
አወቁብኝ መሰል በዛ መደንገጤ
ሽሽጉን ስምሽን ቢጠሩ ቢያወሱ
የምይዘው ጠፋኝ እኔ መላ ቢሱ
መለኛ ነሽ አሉ መቼም መላ አይገድሽ
እስኪ ስጪኝ መላ አትሸሽጊኝ እባክሽ
መቼም መለኛ ነሽ እስኪ ጀባ በይኝ
እቴ ከማክዳሽ ከእልፍኝሽ አውይኝ
♪
ዐይኔ እየዋለለ ተጋልጦ ሚስጥሬ
አደባባይ ወጣ በመላ ማፍቀሬ
ሰበብ ሲቸግረኝ ሲጠፋብኝ ሁሉ
እርጂኝ አትሸሸጊኝ አንቺ መላ ሙሉ
አንቺ መለኛ ሰዉ ሳይጠፋሽ ብልሀቱ
ምን ያደርግልሻል ልቤን ማባባቱ
አንቺ መላ አዋቂ መች ሰበብ ታጫለሽ
ነይልኝ ናፋቆቴ እንደሚሆን ብለሽ
♪
መለኛ ነሽ አሉ መቼም መላ አይገድሽ
እስኪ ስጪኝ መላ አትሸሽጊኝ እባክሽ
መቼም መለኛ ነሽ እስኪ ጀባ በይኝ
እቴ ከማክዳሽ ከእልፍኝሽ አውይኝ
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri