ወጣቷን ልጅ ልቤ የፈለጋት
እንዴት ብዬ በየት ላግኛት
ሆዴ በጣም ውስጤ የናፈቃት
ወጣቷን ልጅ በየት ላግኛት
ንገሩልኝ ሰርቄ ላውጣት
አቤት ውበት ማነው የሰጣት
ስወድሽ አንቺ እንዲ ከቀለድሽ
በፍቅር ከሳቅሽ እንዴት ትዘልኪያለሽ
እረ ተይ ለፍቅር ጊዜ ስጪው
በፌዝና በሳቅ አትለውጪው
አንቺን ሳይ ሁሉም ይጠፋኛል
እንዴት ላውራሽ ግራ ይገባኛል
እረ ተይ ይግባሽ የኔ ችግር
መሳቁ ይቅር ተገዚ ለፍቅር
ወጣቷን ልጅ ልቤ የፈለጋት
እንዴት ብዬ በየት ላግኛት
ሆዴ በጣም ውስጤ የናፈቃት
ወጣቷን ልጅ በየት ላግኛት
ንገሩልኝ ሰርቄ ላውጣት
አቤት ውበት ማነው የሰጣት
አንቺ ልጅ ውስጤ ትኖሪይለሽ
ሚስጥሬ ገብቶሽ ቀድመሽ ቀልቤን ወሰደሽ
በኔ ላይ ፍቅሯ በረታብኝ
ንገሩልኝ ሰዎች ተፋረዱኝ
ከሌላ እየሳቀች መታ
ከኔ ጋራ ፊቷ አይፈታ
ብጠይቅ ፍርዱንስ ከዳኛ
ዘዴውን ባውቅ የልቤን መፅናኛ
ስወድሽ አንቺ እንዲ ከቀለድሽ
በፍቅር ከሳቅሽ እንዴት ትዘልኪያለሽ
እረ ተይ ለፍቅር ጊዜ ስጪው
በፌዝና በሳቅ አትለውጪው
አንቺን ሳይ ሁሉም ይጠፋኛል
እንዴት ላውራሽ ግራ ይገባኛል
እረ ተይ ይግባሽ የኔ ችግር
መሳቁ ይቅር ተገዚ ለፍቅር
ወጣቷን ልጅ ልቤ የፈለጋት
እንዴት ብዬ በየት ላግኛት
ሆዴ በጣም ውስጤ የናፈቃት
ወጣቷን ልጅ በየት ላግኛት
ንገሩልኝ ሰርቄ ላውጣት
አቤት ውበት ማነው የሰጣት
አቤት ውበት ማነው የሰጣት
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
(ማነው የሰጣት?)
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
አቤት ውበት
(ማነው የሰጣት?)
Поcмотреть все песни артиста
Sanatçının diğer albümleri