Kishore Kumar Hits

Dibekulu - Selam şarkı sözleri

Sanatçı: Dibekulu

albüm: Yetu Gar Neh?


ሲነፍስባት የጥሩ ተክሎች መዓዛ
ሲታይባት የወጎች ጣዕም እና ለዛ
አእዋፋቱ በሰማይዋ ላይ ሲበሩ
ከአለም በፊት የሰላም ጌጦች ነበሩ
ንፁህ አየሯ ጎብኚዋን ሁሉ ሲያሳሳው
ሲማርከው የዱር አራዊት እንስሳው
የእኛን አህጉር ምነው ነፈጏት ከስሙ
በምድራችሁ ብለውን መልካም አትዝሩ
(ሰላም ይስፈን በአፍሪካ)
ሺህ ዘመን አርፈናል
(ፍቅር ይዘን እንፍካ)
እድገት ስንቴ ያልፈናል
(እራስ መውደድ ይራቀን)
ሲንቁን እያየን
(እንድናገኝ ቀና ቀን)
ለመንቃት ዘገየን

መጠፋፋት ሲጎዳን ኖሯል ሲያጠቃን
በድህነት ለብዙ ውድቀት ሲያበቃን
ጠብመንጃውን ቀጥቅጠህ ሰርተህ ማረሻ
ልማታችን ይሁነን ለኛ መካሻ
ይነገራል ታሪኳ በሽህ ዘመናት
አፍሪካችን የጥቁር አልማዝ ምንጭ ናት
የሎሚ እሸት አርገናት እፅ መአዛ
በዙሪያዋ ማራኪ ሽታዋን ታብዛ
(ሰላም ይስፈን በአፍሪካ)
ሺህ ዘመን አርፈናል
(ፍቅር ይዘን እንፍካ)
እድገት ስንቴ ያልፈናል
(እራስ መውደድ ይራቀን)
ሲንቁን እያየን
(እንድናገኝ ቀና ቀን)
ለመንቃት ዘገየን
አድሮም ውሎም ያጣጣለን ሆኖ ቀበኛ
የአሁኑ አለም እረሳው ወይ መቆሙን በኛ
በባርነት እያሰረ እንዳላጋዘን
በላባችን ሀገር ሰርቶ መች ዞሮ አገዘን
ምክንያት ፈጥሮ የሚያናንቀን ይህ ሰበበኛ
በራስ መኩራት እንዳይሰማን ሲያድም ነው በኛ
ካከበረን የት እንደምንደርስ ያቀዋል እና
ቢያጣላንም ወድቀን አንቀርም እውነት አለና
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ
አቶቢሲ ማሞ ካቻ
ውጅን ኢንዴምና ገብረ ጉራቻ

Поcмотреть все песни артиста

Sanatçının diğer albümleri

Benzer Sanatçılar